የብርጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ ፋውንዴሽን የጄነራል መኮንኑን የምንጊዜም ወደር የሌለው ጀግና ሜዳይ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስረከበ

የብርጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ ፋውንዴሽን የጄነራል መኮንኑን የምንጊዜም ወደር የሌለው ጀግና ሜዳይ በተጨማሪ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶችም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስረክቧል።

BG Legesse Tefera.jpg

Credit: Supplied

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ትውልድ ከታሪክ የሚማርበትን የኢትዮጵያ ጀግና የብርጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራን የክብር ቅርሶች የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም በቅርስነት መረከቡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን አንጋፋነትና ሀገራዊ ሀላፊነት ያመለክታል በማለት ገልፀዋል።


አሁን ያለውና ተተኪው ትውልድ ይማርበት ዘንድ የወንድሜን ታሪካዊ ቅርሶች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም አስረክቤያለሁ ሲሉ ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ተፈራ የብርጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ ፋውንዴሽን መስራች መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።



የምንጊዜም ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ የሆኑት የአየር ኃይል ጀት አብራሪው የብርጋዲየር ጄነራል ለገሠ የማዕረግ አልባሳት፣ ሜዳሊያዎች እና ልዩ ልዩ ታሪካዊ ቅርሶች፥ አርበኞች፣ ተጋባዥ እንግዶችና የጄነራል መኮንኑ ቤተሰቦች በተገኙበት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተሰጥተዋል።




Share

Published

Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service