ሕወሓት ከአሸባሪነት ተሰረዘ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር በት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባው በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረውን ሕወሓት ከአሸባሪነት ዝርዝር በአብላጫ ድምጽ ሰርዟል።

Members of the Ethiopian Parliament.jpg

Members of the Ethiopian Parliament. Credit: AMANUEL SILESHI/AFP via Getty Images

የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም እንደሚረዳ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ ፍረጃውን ያነሳው የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ሲሆን፤ በስምምነቱ አንቀጽ 7/2 C መሰረት የፌዴራል መንግሥት በህወሓት ላይ የተጣለውን የሽብርተኝነት ስያሜ በምክር ቤቱ እንዲነሳ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ሕወሓትን አሸባሪ ብሎ መሰየሙ ይታወሳል።

የፌዴራል መንግሥትና ሕወሓት ጥቅምት 2015 ዓ.ም ላይ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ለ10 ቀናት ድርድር ካካሄዱ በኋላ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ጥቅም ባስከበረ መልኩ ስምምነት መፈጸማቸው ይታወቃል።

ፓርላማው ውሳኔውን በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈው 61 የተቃውሞና አምስት ድምፀ ተዐቅቦ ገጥሞት ነው።



Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service