አውስትራሊያውያን በመላ አገሪቱ 106ኛውን የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሠራዊት ኮሮች ጋሊፖሊን የረገጡበትን ቀን ከ2019 ወዲህ ዛሬ እሑድ ኤፕሪል 25 በአደባባይ ታድመው ዘከሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ዛሬ ንጋት ላይ በካንብራ የአውስትራሊያ የጦርነት መታሰቢያ ተገኝተው የዝክረ መታሰቢያ ንግግር አድርገዋል።
አቶ ሞሪሰን በንግግራቸው ዕለቱን ከአውስትራሊያ ብሔራዊ ታሪክ ምዕራፍነት ጋር አያይዘው ገልጠዋል።
አክለውም፤
"አገሪቱን አፍጋኒስታን ውስጥ ያገለገሉ ሴቶችና ወንዶች ልጆች፣ ባለቤቶች፣ ፍቅረኞች፣ ወላጆችና ዘመድ አዝማዶች፤ እንዲሁም አገር ውስጥና ባሕር ማዶ ያገለገሉ ቤተሰቦችን ሁሉ በክብር እናስባለን። የእነሱ ፍቅር፣ አበረታችነትና ፀሎቶች ወታደሮቻችን፣ ባሕረኞቻችን፣ የአየር ኃይሎቻችን፣ ነርሶቻችንና ሰላም አስከባሪዎቻችን ጸንተው እንዲቆዩ አግዟል" ብለዋል።
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሚያዝያ 16 - 2013 ወቅታዊ አገራዊና ቀጠናዊ፣ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት እንዲያስጠብቁ፤ ወደማይቀለበስ ከፍታ ለማድረስም እንዲነሱ ጥሪ አድርጓል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው ላይ "ከሦስት ዓመታት በፊት ወደ ለውጥ ጎዳና የገባነው በመንገዱ ላይ ችግሮች አይገጥሙንም በሚል እሳቤ አልነበረም፡፡ ሀገራችን ትከሻ ላይ የተቆለለውን የበዛ ችግር ከነውስብስብነቱ ተረድተን እንጂ፤ አቅልለን አይተን አልተነሳንም... ይሄንን በሚገባ አውቀን እስከ መጨረሻው ሕቅታ ዋጋ ለመከፈል ቆርጠን ነው የተነሳነው" ሲልም ለችግሮች ግንዛቤ፤ ለመፍትሔው ዕሳቤ ያለው መሆኑን አመላክቷል።
አያይዞም፤ ኢትዮጵያውያን ሶስት ወሳኝ ዓላማዎችን በጽናት ማሳካት እንዳለባቸው ሲያሳስብ፤

Source: PMOE
- በመጀመሪያ አንድ ወር ያህል ጊዜ የቀረውን ምርጫ ውጤታማ እናድርገው
- ሁለተኛ ከምርጫው ጎን ለጎን ግድባችንን ባቀድነው መንገድና ጊዜ መገንባትና ሁለተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት ማከናወን አለብን
- እንዲሁም ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቿ ታድገን ወደሚገባት ደረጃ ለመውሰድ እንድንቸል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በንቃትና በብስለት ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን
ብሏል።