የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በ2032 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ብሪስበን - አውስትራሊያ ላይ እንዲካሄድ ከሚያስችል ውሳኔ ላይ ደርሷል።
የኮሚቴው ፕሬዚደንት ቶማስ ባኽ ትናንት ረቡዕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ውሳኔው ማንንም አካል የሚጻረር አይደለም" ብለዋል።
ይህም ማለት ዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴው በተለይ ከአውስትራሊያ መንግሥት ጋር ብሪስበንን "በተመራጭ አስተናጋጅነት ደረጃ" ይደራደራል ማለት እንደሆነ አስረድተዋል።
ይህንንም የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ውሳኔ የአውስትራሊያ ኦሎምፒክ ቡድን በመልካምነቱ ተቀብሎታል።

ብሪስበን ላይ እንዲካሄድ የታሰበው የ2032 ኦሎምፒክ የሚካሄድ ከሆነ አውስትራሊያ ለሶስተኛ ጊዜ የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን የማስተናገድ ዕድል ታገኛለች። ቀደም ሲልም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበትን የ1956 ሜልበርን ኦሎምፒክ ጨምሮ በ2000 የሲድኒ ኦሎምፒክ ጨዋታዋችን አስተናግዳለች።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ሰባት ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው መዘገብ እንዲችሉ ፈቃድ ተሰጥቷል።
ለዘገባው ፈቃድ የተሰጣቸው፤
- ኒውዮርክ ታይምስ
- አልጀዚራ
- ሮይተርስ
- ቢቢሲ
- ፍራንስ 24
- ፋይናንሽያል ታይምስና
- ኤ.ኤፍ.ፒ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ በትግራይ ከአንድ ሳምንት በላይ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ስርጭት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን አስታውቋል።
የኃይል ስርጭቱ ተቋርጦ የነበረውም በቀድሞው ሕወሓት ታጣቂዎች አዲጉዶም በተባለ አካባቢ ከአላማጣ መሆኒ መቀሌ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ጥቃት እንደነበረ ገልጧል።
በማኅበራዊ ሚዲያ፣ ኦንላይንና በአየር ሞገድ እንደምን እንደሚያገኙን መንገዶቹን እነሆ።
በቲዊተር @SBSAmharic ይከተሉን።
በዩቲዩብ www.youtube.com/user/SBSAmharic ያድምጡን።
ሬዲዮ
SBS አማርኛን ከምሽቱ 10pm ጀምሮ ዘወትር ሰኞ እና ዓርብ በ SBS ሬዲዮ 1ያድምጡ።
የኛን tune in page በመጎብኘት የአካባቢዎን የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ፈልገው ያግኙ። Melbourne - 93.1FM
በ digital radio ለማድመጥ ‘SBS Radio’ ን ተይበው ይፈልጉ።
ፖድካስት
SBS አማርኛን በ Spotify, Apple Podcasts እና Google Podcasts ያድምጡ።
SBS ሬዲዮ ኣፕ
SBS ራዲዮን በቀጥታ እንዲሁም ፖድካስቶችን ከአንድ ቦታ ለማድመጥ SBS Radio appን ዳውንሎድ ያድርጉ።
ቴሌቪዢን
SBS አማርኛን በቀጥታ በ television station SBS ሬዲዮ 1, በቻናል 37 እና 301 ያድምጡ። ለተጨማሪ መረጃ listen via television page ይጎብኙ።

