ተቋሙ ዓላማና ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት በማሰብ መተግበሪያውን ማበልጸጉን ይፋ አድርጓል።
በባለፉት አሠርት ዓመታት በልጆች ዙርያ የተለያዩ ሥራዎች ሲሠራ የቆየው ተቋሙ በባለፉት ሰባት ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ያስመረቀው ይህ መተግበሪያ በውስጡ 10 የሚሆኑ ይዘቶችን ማካተቱ ተገልጧል።
መተግበሪያው ያበለጸገው መሁቡብ ቴክኖሎጂስ መተግበሪያው ለልጆች አመቺ የሆነና አጠቃቀም ተብሎ ቀለል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ ሕብስት አሰፋ እንደተናገሩት በተመደቡበት የሥራ ዘርፍ ተሰልፈው ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ምስጋና ይግባና ዛሬ ለዚህ በቅተናል ብለዋል።
"ተቋማችን እዚህ የመድረሱ ምስጢር የልጆቻችን ወላጆች ናቸው" ያሉት ሥራ አስኪያጇ "ስላደረጋችሁት ሁሉ ነገር እናመሰግናለን" ብለዋል።