የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በይፋዊ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይእንደገለፁት፤
“የቴሌ ክላውድ አገልግሎት ተቋማት የራሳቸው የመረጃ ማዕከል እንዲሁም ለማዕከሉ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን መገንባት ሳያስፈልጋቸው ካሉበት ሆነው የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል መፍትሄ አቅራቢዎች ዓለም በደረሰባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቅመው በገነቧቸው እና ደህንነታቸው በተጠበቁ የመረጃ ማዕከላት መረጃዎቻቸውን ማከማችት፣ መቀመር እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል ነው” ብለዋል።
ፍሬሕይወት አክለውም የቴሌ ክላውድ ዲጂታል አገልግሎት ድርጅቶች እና ተቋማት ለቴክኖሎጂ መረጣ እና ለስልጠና የሚወስደውን ጊዜ እና የውጪ ምንዛሬ ክፍያ እንደሚያስቀር ገልጸዋል።
የቴሌ ክላውድ ዲጂታል አገልግሎት በሶስት ዓመት የሊድ ስትራተጂ ይሰራሉ ከተባሉ የዲጅታል አገልግሎቶች አንዱ መሆኑን አሳውቀዋል ስራ አስፈጻሚዋ።
[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]