በምክር ቤቱ ውሳኔም መሠረት መሪ ቃሉ "ጳጉሜን በመደመር" የሚል መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ ከበደ ደሲሳ አስታውቀዋል።
አቶ ከበደ አያይዘውም፤ ለዕለታቱ የተሰጧቸውን ስያሜዎች ገልጠዋል።
በዚህም መሠረት፤
ጳጉሜን 1 - የበጎ ፈቃድ ቀን
ጳጉሜን 2 - የአምራችነት ቀን
ጳጉሜን 3 - የሰላም ቀን
ጳጉሜን 4 - የአገልጋይነት ቀን
ጳጉሜን 5 - የአንድነት ቀን ተብለው ተሰይመዋል።
በእያንዳንዱ የጳጉሜን ቀን ከስያሜው ጋር የተገናኙ መርሃ ግብሮችና ክንዋኔዎች የሚካሔዱ ሲሆን፤ ግብሮቹ የሚከወኑትም በሰላም መደፍረስ ባልታወኩ የኢትዮጵያ ከፍለ አገራት በሙሉ በተመሳሳይ መልኩ ይሆናል።