የአውስትራሊያ የድርጊት ወዳጅነት ይፋ ባደረገው የስድስት ወራት ሪፖርት በምሥራቅ አፍሪካ ከ 46.3 ሚሊየን ሰዎች በላይ ለምግብ እጥረት ተዳረው ያሉ እንዳሉና ድርቅና ግጭት ለክስተቱ አስባብ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ምግብና ውኃ ፍለጋ ከቀዬአቸው ርቀው የሚሄዱ ተፈናቃዮች ከሌሎች የአካባቢው ሰዎች ጋር ለግጭት ለመዳረግ እንዳበቃቸውም ገልጧል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለአምስት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች እጥረቶች መከሰት ሁኔታውን ያባብሰው መሆኑንና ቀውሱ ከጎዳቸው ሁለት ሶስተኛዎቹ ሴቶችና ሕፃናት እንደሆኑ አመልክቷል።
የዓለም ምግብ ድርጅት በበኩሉ በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች በተከሰቱት ግጭቶች ሳቢያ 9 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያሻቸው፣ ድርቅ በፈጠረው ረሃብ ሳቢያም በመላ ኢትዮጵያ 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ሕዝብ ለረሃብ መጋለጡን አስታውቋል።