አውስትራሊያውያን ነርሶች በዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን በአውስትራሊያውያን ምሥጋና ተበረከተላቸው

ነርሶች በመላው ዓለም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን እየተፋለሙ ካሉት የጤና ሠራተኞች ውስጥ በግንባር መስመር ተሠልፈው ያሉና ቀዳሚ ተጠቃሽም ናቸው። አውስትራሊያም 'ለግልጋሎታችሁ እንመሰግናለን' ስትል ነርሶቿን በዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን ሞገስ አላብሳቸዋለች። አውስትራሊያውያን በቪዲዮ መልዕክቶቻቸው፣ በሙዚቃ ቅንብራቸውና በአካልም በየሥራ መደባቸው 'እናመሰግናለን' ሲሉ ልባዊ አድናቆታቸውን ቸረዋቸዋል።

Australia thanks nurses

Source: Getty Images

አካላዊ ርቀቶቻቸውን ጠብቀው ምሥጋናቸውን ለነርሶች ካቀረቡቱ ውስጥ አያሌ የአረጋውያን መጦሪያ ቤቶች ተጠዋሪዎች ይገኙበታል።

'ያለመታከት በየዕለቱ ላደረጋችሁልን ልባዊ  ክብካቤ ልባዊ ምስጋናችንን እነሆን' ብለዋል። 

 ከዩጎዝላቪያ በ1992 መጥተው ለነርስ ዳይሬክተርነት የበቁት ኢቫ ቤልላይ በተለይም በአረጋውያን መጦሪያ ላሉ ነርሶች ከኮቪድ - 19 ጋር ተፋልሞ እያካሄዱ የአረጋውያኑን ሕይወት የመታደጉ ተግባር እጅጉን ፈታኝ እንደነበር ተናግረዋል። 

የአውስትራሊያ ዋና የነርስና አዋላጅ መኮንን - ኤሊሰን ማክሚላን አውስትራሊያውያን ማኅበራዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ ለነርሶች ምሥጋናቸውን እንዳቀረቡት ሁሉ፤ 'በዚሁ በመቀጠል ደህንነታችንን እንዲጠብቁልን በመላው የአውስትራሊያ የጤና ሠራተኞች ስም መልዕክቴን ማስተላለፍ እሻለሁ' ሲሉ አደራ ብለዋል።

 በየዓመቱ ሜይ 12 የዘመናዊ ነርስ መሥራቿን ፍሎረንስ ናይቲንጌልን ዕለተ ልደት በመዘከር የሚከበረው ዓለም አቀፉ ዝክረ በዓል ዛሬ 200ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል።
Australia thanks nurses
Florence Nightingale Source: Courtesy of PD
የቀድሞዋ ነርስና የአሁኗ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር ሄለን ሃይነስ - ፍሎረንስ ናይቲንጌል ለመላው የጤና ሠራተኞች የማለፊያ ተግባር አብነት ናት ሲሉ በውዳሴ ቃላቸው የዝክረ መታሰቢያውን ፋይዳ አመላክተዋል።

ዶ/ር ሃይነስ እንደ ፍሎረንስ ናይቲንጌል ሁሉ በየአረጋውያን መጦሪያዎች፣ ሆስፒታሎችና የማገገሚያ ማዕከላት ሁሉ ግልጋሎታቸውን በአይታክቴነት የሚያበረክቱት 390,000 አውስትራሊያውያን ነርሶች ፍሎረንስ ናይቲንጌል እንደሆኑ የሙያ ተወራራሽነትና የመልካም ግብር ተምሳሌነታቸውን አሰናስለው ነቅሰዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም ምሥጋናቸውን ሲገልጡ፤

"እናንት ለሕሙማን ደራሽ፤ ለእኛ አለሁ ባዮች ናችሁ። በዚህ ወቅት፤ የአገራችንን ሕይወት ታድጋችሁ እዚህ እንድንደርስ ያበቃችሁን ናችሁና - እናመሰግናለን" ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅትም በበኩሉ 2020ን 'ዓለም አቀፍ የነርስና አዋላጅ' ዓመት ሲል ሰይሟል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ መረጃ ካሹ  sbs.com.au/coronavirus ድረ - ገፃችንን ይጎብኙ።

 


Share

Published

Updated

By Cassandra Bain
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service