አውስትራሊያ ክፍለ አገራት ውስጥ ከሜይ 1 ጀምሮ የላሉ ገደቦች

በኮቪድ - 19 አስባብ ተጥለው የነበሩ ገደቦች በመርገባቸው ሚሊየን አውስትራሊያውያን በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ከየቤቶቻቸው ወጣ ብለው በከፊል ለቀቅ ያለ ሕይወትን ማጣጣም ይጀምራሉ። ይሁንና የላሉት ገደቦች በየስቴትና ክፍለ ግዛቱ የተለያዩ ናቸው።

Australia's coronavirus restrictions are easing.

Australia's coronavirus restrictions are easing. Source: AAP

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

  • ከሜይ 1 ጀምሮ "ማኅበራዊ ገለልተኝነትን ለመቀነስና የአዕምሮ ጤናን ለመጠበቅ" ሁለት አዋቂ ሰዎች ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ሌሎች ሰዎች ዘንድ ሔደው መጠያየቅ ይችላሉ።
  • በጉብኝታችው ወቅት አካላዊ ርቀትና ተጨማሪ ሥነ ንጽሕናን መጠበቅ ይኖርባቸዋል።
  • ቦንዳይና ብሮንቴን የመሳሰሉ የሲድኒ ዝነኛ የውቅያኖስ ዳርቻዎች ለዋናና ቀዘፋ ብቻ ክፍት ይሆናሉ።
  • ከጎረቤት ወይም ዘመድ አዝማድ ጥየቃ ባሻገር ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቅቀው ለመውጣት የሚችሉት ለምግብ ወይም ሌሎች ቁሳቁሶች ሸመታ፣ ግልጋሎቶችን ለመጠቀም፣ ወደ ሥራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት ለመሔድ፣ ለአካላዊ እንቅስቃሴ፣ ለሕክምና ወይም ለሌሎች ክብካቤ ለማድረግ የመሰሉ በቂ ምክንያቶች ሲኖሯቸው ይሆናል።  
Australia's coronavirus restrictions are easing. Here's what you can do in your state this weekend
COVID - Driving Source: SBS
ኒው ሳዝ ዌይልስ ውስጥ በየጊዜው የሚለወጡትን ደንቦች ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ። https://www.nsw.gov.au/covid-19/what-you-can-and-cant-do-under-rules

ኩዊንስላንድ

  • ከሜይ 1 ጀምሮ ነዋሪዎች ለሽርሽር ከቤታቸው መውጣት ይፈቀድላቸዋል፤ ቀደም ሲል አላስፈላጊ ተብለው ገደብ ተጥሎባቸው ወደ ነበሩ መኪና የማሽከርከሪያ ሥፍራዎች መሔድ ይቻላል፣ ለመዝናኛ ሞተር ብስክሌትና ጄትስኪ መንዳት፣ ጀልባ ቀዘፋ፣ ብሔራዊ ፓርክ ጉብኝትና ቀደም ሲል አላስፈላጊ ተብለው የነበሩ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ወደ ገበያ መሔድ ይችላሉ።
  • ነዋሪዎች ከቤታቸው 50 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውጪ መሔድ አይችሉም። የሚያደርጓቸውንም እንቅስቃሴዎች ማድረግ የሚችሉት አንድ ቤት ውስጥ አብረዋቸው ከሚኖሩት ሰዎች ጋር ብቻ ይሆናል። ላጤ ከሆኑ ከአንድ ተጨማሪ ሰው ጋር ብቻ ማኅበራዊ ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ።
  • አካላዊ ርቀት  በ 1.5 ሜትሮች እንዲሁም ሥነ ንጽሕና የግድ መጠበቅ ይኖርባቸዋል።
በኩዊንስላንድ የሚካሔዱ የገደብ ለውጦችን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ። https://www.covid19.qld.gov.au/

ኖርዘርን ቴሪቶሪ

  • ከሜይ 1 ጀምሮ የመጫወቻ ሥፍራዎች፣ የሕዝብ መዋኛ ቦታዎች፣ የተወሰኑ ብሔራዊ ፓርኮች ክፍት ከሚሆኑት ውስጥ ሲሆኑ፤ ከወዳጆች ጋር ሆኖ ዓሣ ጠመዳዎችን ማድረግና ጎልፍ መጫወት ይፈቀዳል።
  • የሰውነት እንቅስቃሴ መሥሪያዎች፣ ካፌዎች፣ ምግብ ቤቶችና መጠጥ ቤቶች በሁለት ሰዓት የቆይታ ገደብ በሜይ 15 ክፍት ይሆናሉ።
  • ከጁን 5 ጀምሮ የኮቪድ - 19 ዕቅድን ተከትሎ የንግድ ተቋማት ክፍት ይሆናሉ፤ ተመልካቾች በስፖርት ሥፍራዎች መታደም ይችላሉ።
  • ሆኖም አካላዊ ርቀትን በ 1.5 ሜትሮች መጠበቅ ያልተነሳ ገደብ ስለሆነ በንግድ ተቋማቱም ሆነ በስፖርት ሥፍራዎች መመሪያዎቹን መተግበር ግድ ይላል። 
የኖርዘርን ቴሪቶሪን የገደብ ለውጦች ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ። https://coronavirus.nt.gov.au/home

ምዕራብ አውስትራሊያ

  • ከ 10 ያልበለጡ ሰዎች ተሰባስበው የአካል እንቅስቅሴዎችን ማድረግ፣ ሠርግ ላይ መታደምና የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘት ይችላሉ።
  • ሰዎች የጉዞ ገደቦችን ሳይጥሱ ወደ ፓርኮች ሄደው መንሸራሸር፣ ዓሣ ማስገር፣ ጀልባዎችን መቅዘፍ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ተፈቅዶላቸዋል።
  • መንግሥት ቡና ቤቶችንና ምግብ ቤቶች እንዲከፈቱ ለማድረግ እየተሰናዳ በመሆኑ የመስተንግዶ ሠራተኞች የኮቪድ - 19 ሥነ ንጽሕና ኮርሶችን ማጠናቀቃቸውን ይቆጣጠራል።
የምዕራብ አውስትራሊያን የገደብ ለውጦች ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ። https://www.wa.gov.au/organisation/department-of-the-premier-and-cabinet/covid-19-coronavirus-community-advice#social-distancing

ቪክቶሪያ 

  • ቪክቶሪያ ውስጥ ተጥሎ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሜይ 11 እስከሚያበቃ ድረስ የሚደረግ ለውጥ የለም።
በቪክቶሪያ የሚደረጉ የገደብ ለውጦችን ለመከላከል ሊንኩን ይጫኑ። https://www.vic.gov.au/coronavirus-covid-19-restrictions-victoria

ደቡብ አውስትራሊያ

  • አዲስ ለውጦች አልተካሔዱም።
  • በሌሎች ክፍለ አገራት ጥብቅ ገደቦች ተጥለው ባሉት ወቅት ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ የላላ ስለነበር እስከ 10 ሰዎች መሰባሰብ ይችላሉ። የኮሮናቫይረስ ገደቦችን ተላልፈዋል በሚል መቀጮ ያገኛቸው ሰዎችም የሉም። 
በደቡብ አውስትራሊያ የሚካሔዱ የገደብ ለውጦችን ለማወቅ ሊንኩን ይጫኑ። https://www.covid-19.sa.gov.au/home/dashboard

 

ታዝማኒያ

  • የተካሔደ አዲስ ለውጥ የለም።
  • በሰሜን - ምዕራብ ጥብቅ ገደቦችን የጣለችዋ ታዝማኒያ ከቪክቶሪያ ጋር ተመሳሳይ አቋም ይዛ አለች።
በታዝማኒያ የሚካሔዱ የገደብ ለውጦችን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ። https://www.coronavirus.tas.gov.au/facts/important-community-updates

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

  • አዲስ ለውጥ አልተነገረም።
  • በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የሚካሔዱ የገደብ ለውጦችን ለማወቅ ሊንኩን ይጫኑ። https://www.covid19.act.gov.au/

Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
አውስትራሊያ ክፍለ አገራት ውስጥ ከሜይ 1 ጀምሮ የላሉ ገደቦች | SBS Amharic