የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር ተለወጠ

*** ከዛሬ ጃኑዋሪ 1, 2021 ጀምሮ በይፋ ይዘመራል።

Australia's National Anthem

Himno australiano se escucha en partido de rugby. Source: AAP

የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር ከዛሬ ጃኑዋሪ 1, 2021 ጀምሮ ተለወጧል።

ጠቅላይ እንደራሴ ዴቪድ ሃርሌይ የአውስትራሊያ "Advance Australia Fair" ብሔራዊ መዝሙር ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ተስማምተዋል።

የማሻሻያ ለውጡ የተደረገው  በብሔራዊ መዝሙሩ ሁለተኛ መስመር ላይ ከ ‘For we are young and free’ ወደ  ‘For we are one and free.” ለውጥ በማድረግ ነው።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ለውጡ የተደረገው ለሁሉም አውስትራሊያውያን መሆኑንና አንድነትን የሚያንጸባርቅ እንደሆነ ጠቁመው "አውስትራሊያ እንደ ዘመናዊ አገር ወጣት ብትሆንም፤ የአገራችን ታሪክ ግና ጥንታዊ ነው" ብለዋል። 

አክለውም "በአንድነት መንፈስ ብሔራዊ መዝሙራችን እውነትንና የጋራ የሆነ አድናቆትን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነገር ነው። "ወጣትና ነፃ - young and free" የሚለውን ወደ "አንድና ነፃ - one and free" መለወጡ የሚቀንሰው አንዳችም ነገር የለም፤ ከቶውንም አብዝቶ ይጨምራል እንጂ" ሲሉ የብሔራዊ መዝሙሩን መለወጥ አስፈላጊነትና ዋጋ ገልጠዋል።

 አውስትራሊያውያን ባለፈው ዓመት ያሳዩትን ጥንካሬና አንድነት አድንቀው "ከሌሎች አገራት በላቀ ለስኬት ያበቃን አንድነታችን ነው" ብለዋል።

የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር 'Advance Australia Fair' ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፈው በስኮትላዳዊው ፒተር ዶድስ ማክኮርሚክ ነው።

ማክኮርሚክ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ለሁለት ጊዜያት በ1901 እና በፌዴሬሽኑ ምሥረታ ወቅትና በ1914 በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የብሔራዊ መዝሙሩን ስንኞች ቀይረዋል። ለክለሳ የበቁትም "Australia's sons let us rejoice" እና "Britannia rules the wave" የሚሉት ነበሩ።

በአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር ላይ ብርቱ ለውጥ የተደረገው በጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሆውክ አስተዳደር ወቅት በ1984 በብሔራዊ መዝሙሩ ላይ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ከተሰጠበት በኋላ ነው። የሕዝበ ውሳኔው ውጤት ተከትሎም  'God Save the Queen' በ 'Advance Australia Fair' ተተክቷል።

አዲሱ የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር

Australians all let us rejoice,

For we are one and free;

We’ve golden soil and wealth for toil;

Our home is girt by sea;

Our land abounds in nature’s gifts Of beauty rich and rare;

In history’s page, let every stage Advance Australia Fair.

In joyful strains then let us sing, Advance Australia Fair.

 

Beneath our radiant Southern Cross We’ll toil with hearts and hands;

To make this Commonwealth of ours Renowned of all the lands;

For those who’ve come across the seas We’ve boundless plains to share;

With courage let us all combine To Advance Australia Fair.

In joyful strains then let us sing, Advance Australia Fair.

 

 

 

 

 


Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የአውስትራሊያ ብሔራዊ መዝሙር ተለወጠ | SBS Amharic