ኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ለተመላሽ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች አሽኛኘት አደረጉ

*** ለተሰናባች ዲፕሎማቶች ከማኅበረሰቡ አባላት የተዘጋጁ ሽልማቶች ተበርክተዋል።

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

በአገረ አውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ - ኢትዮጵያውያን ዛሬ ኦገስት 8 ከምሽቱ 7:00pm ጀምሮ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በባሕር ማዶ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ የተደረገላቸውን ጥሪ ተከትሎ የአሸኛኘት ዝግጅት አድርገዋል። 

በዝግጅቱ ሂደትም ለተሰናባች ዲፕሎማቶች ከማኅበረሰቡ አባላት የተዘጋጁ ሽልማቶች ተበርክተዋል።
SBS Amharic
L-R Gizachew Addis, Beryihun Degu, Ambassador Dr Kedir Muktar and Merhawit Hadish. Source: SBS Amharic
 

ዝግጅቱን አስመልክቶ በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር ባደረጉት ንግግር "ይህ በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብና ኤምባሲ መካከል የተፈጠረው ቤተሰባዊ ትስስር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። እዚህም እንኑር ወደ ሌላም ቦታ እንሂድ ሁሌም ከልባችን እንዳይጠፋ ነው ያደረጋችሁን" ብለዋል።

አያይዘውም የዲፕሎማቶቹ ወደ አገር ቤት መመለስ ቀጣዩ የኤምባሲውና የማኅበረሰቡ አባላት ግንኙነትና ግልጋሎቶች ምን ሊሆን ይችላል የሚል ዕሳቤ ላላቸው ወገኖች ቀጣይ ሁነቶችን በተመለከተ "በእርግጠኝነት የምነግራችሁ መንግሥት በደንብ የታሰበበት አቅጣጫን አስቀምጦ መመሪያዎችን ይልካል። ወቅቱም ሲደርስ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራችሁና ግልጋሎትም የምታገኙበትን እናስረዳለን። ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ተኪ የሌለው አስተዋፅዖ እያደረጋችሁ መሆኑን መንግሥት ዕውቅና ይሰጣል" በማለት ተናግረዋል። 

ተሰናባች የሥራ ባልደረቦቻቸውን አንስተውም " በርካታ ቦታዎች ተዘዋውሬ ሰርቻለሁ። በኤምባሲው ዲፕሎማቶች ዘንድ ያየሁት የኢትዮጵያዊነት ስሜት ሌላ ቦታ አላየሁም። በርካታ ተሞክሮዎችንም አካብተናል። ዲፕሎማት እንደ ወታደር ነው፤ መለያየት ሲመጣ ህመም አለው። ይህ የሚሰማን ቢሆንም አገር በምትፈልገን ቦታ ተሰማርተን መሥራት ግዴታችን ነው። በየትኛውም መስክ፤ በየትኛውም ቦታ መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁዎች ነን" ብለዋል።       

በማጠቃለያ ንግግራቸውም "አንድ ሆነን ከተረባረብን የማንፈታው ችግር የለም። ላደረጋችሁት ዝግጅት በጣም አመሰግናለሁ። በሕዝባዊ ዲፕሎማሲ፣ በሃብት አሰባሰብና በምርምር ዘርፍ ያሉ አደረጃጀቶችን አጠናክራችሁ ቀጥሉ" ሲሉ አበረታተዋል።

የተለያዩ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት ማኅበረሰብ አባላት ተወካዮችም ከዲፕሎማቶቹ ጋር ስለነበራቸው መልካም የሥራ ግንኙነቶች፣ ማሳሰቢያዎችና ሊወሰዱ ስለሚገቡ የማስተካካያ እርምጃዎች ነቅሰው ተናግረዋል። የ "ደህና ግቡ" መልካም ምኞቶቻቸውንም አስተላልፈዋል።   

ተሰናባች ዲፕሎማቶቹም የአጸፋ ምሥጋናቸውን ለማኅበረሰቡ አባላት አቅርበዋል። ከማኅበረሰቡ የተደረጉላቸውን መልካም ድጋፎች አንስተዋል፤ ትውስታዎቻቸውንም አጋርተዋል።  


Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ለተመላሽ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች አሽኛኘት አደረጉ | SBS Amharic