- የቋንቋ ግልጋሎቶች ክለሳ ሂደት በየአምስት ዓመታቱ የሚከናወነው የብሔራዊ ሕዝብ ቆጠራን መሠረት አድርጎ ነው
- ለስድስት ሳምንታት የሚከናወነው ሕዝባዊ ምክክር ከኦክቶበር 5 እስከ ኖቬምበር 12, 2012 ይካሄዳል
- የቋንቋ ግልጋሎቶች ክለሳ ውጤቶች ኦክቶበር 2022 ላይ ይፋ የሚሆን ሲሆን ማናቸውም ለውጦች ኖቬምበር 2022 ላይ ግብር ላይ ይውላሉ
SBS በ1975 የመድብለ ባሕል ብዙኅን መገናኛ ስርጭቱን የጀመረው በስምንት ቋንቋዎች ነው።
እኒያ የስርጭት ጅማሮዎች በቂ ነበሩ፤ ጎዳና ላይ የጫሯቸውንም ድንገተኛ ፈንጠዝያ የኦዲዮና ቋንቋ ይዘት ዳይሬክተር ዴቪድ ሁኣ ያወሳሉ።
"አንድ ቱርካዊ የከባድ ጭነት መኪና ሾፌር የSBS ራዲዮን እያደመጠ ሳለ ለመጀመሪያ ጊዜ አንደበቱን የፈታበትን ቋንቋ በአውስትራሊያ ሚዲያ ሰማ፤ ከከባድ ጭነት መኪናው ወርዶም መጋጠሚያ መንገድ ላይ በደስታ ደነሰ"
አሁን ከ46 ዓመታት በኋላ በተለያዩ የስርጭት መድረኮች SBS ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ስርጭቶቹን ያስተላልፋል።
የመድብለ ባሕልና መድብለ ቋንቋ አውስትራሊያ ፍላጎቶችን ማገልገል
ዋነኛ ዓላማዎቹ ፀንተው ይቆያሉ፤ የመድብለ ባሕልና መድበለ ቋንቋ አውስትራሊያ ፍላጎቶችን ማገልገል።
ዲቪድ ሁኣ "SBS በተለያዩ መዳረሻዎች የአውስትራሊያ ዝንቅ ማኅበረሰባት ዘንድ በመድብለ ቋንቋ ግልጋሎቶቹ የመድረስና መገኛነት ልዩ ክህሎት አለው" ይላሉ።
"ከ45 ዓመታት በላይ ፈጠራና ትርጉም ባለው መንገድ ራሳችንን አዋድደን ዘልቀናል፤ ዛሬ በራዲዮ፣ ኦንላይን፣ ፖድካስት እና ኧፖች አማካይነት ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ግልጋሎቶችን እያበረከትን እንገኛለን።

Cung Khukzawn, a producer with SBS Haka Chin, in an SBS Melbourne studio. Source: SBS/Gareth Boreham
ይህንንም ማለፊያ አድርጎ ለመከወን SBS ራዲዮ በፍጥነት እየተለወጠና እየጨመረ ያለውን የአውስትራሊያ ሕብረተሰብ እንዲያንፀባርቅ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራን ተከትሎ በየአምስት ዓመቱ ክለሳ ያደርጋል።
የዚህ ዓመት ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ በሚቀጥለው ዓመት ጁን ላይ ይፋ ይሆናል።
ዲቪድ ሁኣ ይህም SBS ማኅበረሰቡ እየተለወጠ በሄደ ቁጥር ምን ዓይነት የቋንቋ ግልግሎቶቹን ማቅረብ እንዳለበት እንዲረዳ እንደሚያስችለው ያነሳሉ።
"SBS የለውጥ ሂደቱን ተከትሎ የምናገለግለው ማኅበረሰብ ይበልጥ የሚያስፈልገውን ተስማሚ ግልጋሎቶች ማዋደድ ያሻዋል።"
ክለሳው የSBS ኦዲዮና ቋንቋን ጨምሮ SBS በጥየቃ፣ የፖድካስትና ሌሎች ዲጂታል መድረኮችንም ያካትታል - ይላሉ።
"ክለሳው 50ኛ ዓመቱ ሊያስቆጥር እያመራ ላለው SBS ማነጫነት ያግዛል - ዲቪድ ሁኣ"
በ2018 ሰባት አዳዲስ ቋንቋዎች ለSBS ታክለዋል
ሃካ ቺን - በአብዛኛው የሚነገረው በምዕራባዊ ማያንማር ሪጂን ችሂን ክፍለ አገር ውስጥ ነው፤ በ2018 ሞንጎልኛ፣ ኪሩንዲ፣ ቲቤትኛ፣ ካረን፣ ሮሂንጋና ቴሉጉን ጨምሮ ከታከሉት ሰባት ቋንቋዎች አንዱ ነው።
የሃካ ቺን አዘጋጅ ካንግ ኩክዛውን ከሜልበርን ስቱዲዮ እንደተናገረው SBS የማኅበረሰቡ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ነው።
"የኛ ቋንቋ በSBS መሰራጨት በጭራሽ የማይታመን ማለፊያ ዕድል ነው"
"አብዛኛዎቹ ወላጆቻችን እንግሊዝኛ አይናገሩም ወይም አይረዱም። በቋንቋቸው አውስትራሊያ ውስጥ ምን እየሆነና እየተከናወነ እንዳለ ግና ይረዳሉ” ብሏል።
አዲስና በማደግ ያሉ ማኅበረሰባት
መሐመድ አል-ክሃፋጂ የአውስትራሊያ ዘውጌ ማኅበረሰባት ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አናሳ የማኅበረሰብ ቁጥር ያላቸውን አዲስና በማደግ ላይ ያሉ ማኅበረሰባትን ለማስተናገድ ክለሳ ማድረጉ በእጅጉ ጠቃሚ እንደሆነ ሲናገሩ፤
"SBS አውስትራሊያ በቅርብ ለዘለቁ ስደተኛ ማኅበረሰባት በተለይም አዲስና በማደግ ላይ ላሉ ማኅበረሰባት በእውነቱ በጣሙን ጠቃሚ ነው" ብለዋል።
"እርግጥ ነው ሌሎች ቋንቋዎች ሲቀነሱ ከማየት ይልቅ ተጨማሪ ቋንቋዎች ሲታከሉ ማየትን ነው የምንወደው። አውስትራሊያ ውስጥ ባሕላዊ ዝንቅነት እያደገ ነው፤ SBS ተጨማሪ ቋንቋዎችን ማካተት እንዲችል መንግሥት ተመጣጣኝ ድጎማን ያደርጋል የሚል ተስፋ አለን።"

SBS Arabic24 is just one of the language services produced by SBS. Source: SBS
ዴቪድ ሁኣም በበኩላቸው የSBS መድብለ ቋንቋ ሁነኛ ሚና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ወሳኝ የሆኑ ወቅታዊና የጤና መረጃዎችን ለማኅበረሰባቱ ተመራጭ በሆኑ ቋንቋዎች ማቅረቡን ነቅሰው አመላክተዋል።
"ከ45 ዓመታት በላይ ፈጠራና ትርጉም ባለው መንገድ ራሳችንን እያዋሃድን ለማኅበረሰባት ግልጋሎቶችን እየሰጠን እንገኛለን - ዲቪድ ሁኣ"
አክለውም “በየጊዜው የሚደረጉ ወቅታዊ ማሻሻያዎች SBS ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ የመደብ ጀርባ ላላቸው ትላልቅ ማኅበረሰባት የተሻለ የቋንቋ ግልጋሎት ዕድሎችን እንዲያበረክት ያስችለዋል" በማለት "እንዲሁም በማደግ ላይ ላሉና አስፈላጊነቱ ከፍተኛ ለሆነባቸው ማኅበረሰባት የግልጋሎት በረክቶቹን ያቀርባል" ብለዋል።
ለስድስት ሳምንታት የሚቆየው ሕዝባዊ ምክክር 5 October ጀምሮ ኖቬምበር 12, 2021 ያበቃል።

SBS Gujarati Executive Producer Nital Desai with UNICEF Australia Director of International Programs Felicity Butler-Wever in the Sydney studio. Source: Yutong Ding
ሁሉም ግብረ ምላሽ feedback ሜይ 2022 ለሚጠናቀቀው የመረጣ መመዘኛና እንዲሁም ተከልሶ በ2022 መጨረሻ ግብር ላይ ለሚውለው የSBS ቋንቋ ግልጋሎቶች ግብአትነት ግምት ውስጥ ይገባል።