የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ አውስትራሊያ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሊያልፍ ነው

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 1,247 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ዘጠኝ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።

COVID-19 update

House in the Sydney suburb of Blacktown lit up for Diwali. Source: SBS

ፋይዘር ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ላሉ ልጆች ክትባት መስጠት እንዲችል የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር ይሁንታን ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባቱን የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት አስታወቁ። 

በቀጣይነትም ከአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ይሁንታ እንደተገኘም ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ላሉ ልጆች ክትባት መስጠት ይጀመራል። 

አቶ ሃንት በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ቁጥር 80 ፐርሰንት እንደሚያልፍ ተናግረዋል። 

በሌላ በኩል ኩዊንስላንድ በምትገኘው ጉንዲዊንዲ ከተማ ኮሮናቫይረስ በመከሰቱ የምርመራ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። ይሁንና ከተማይቱ ላይ ገደቦች አልተጣሉም። 

ከዛሬ ጀምሮ የሚካሔደውን የዲዋሊ ክብረ በዓል ተከትሎ የኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕል ጤና ኮሚሽን አገልግሎት የተወሰኑ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥቷል። 

COVID-19 update
Source: NSW Health

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ

  • ቪክቶሪያ ውስጥ 1,247 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ዘጠኝ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 308 በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ዘጠኝ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ሶስት ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ።
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 13 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።

የክትባት አሰጣጥ

የማጠናከሪያ ሶስተኛ ዙር ክትባት ኖርዘር ቴሪቶሪ ውስጥ ከሰኞ ኖቬምበር 8 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል፤ ሆኖም ግዴታ አይሆንም።


1 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now