የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ በቪክቶሪያና ኒው ሳውዝ ዌይልስ መካከል ያሉ ወሰኖች ሙሉ በሙሉ ተከፈቱ

*** በአንድ ሰው በኮቪድ-19 መጠቃት ምክንያት ኖርዘርን ቴሪቶሪ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ናት

COVID-19 update

Flights between NSW and Victoria have resumed without any COVID-19 restrictions, as the border between the two states reopens. Source: AAP

በቪክቶሪያና ኒው ሳውዝ ዌይልስ መካከል ያሉ ወሰኖች ሙሉ በሙሉ ተከፈቱ። ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች ዳግም ተገናኝተዋል፤ በዓለም ካሉ የተጨናንቀ የአየር መስመር አንዱ በሆነው የበረራ መንገድ መንገድ በጢያራ መጓጓዝ ይችላሉ።   

በአንድ ሰው በኮቪድ-19 መጠቃት ምክንያት ኖርዘርን ቴሪቶሪ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ናት high alert በሳቢያውም ለ72 ሰዓታት የሚቆይ ገደብ ተጥሏል። 

የብሔራዊ ካቢኔው ከአምስት ሳምንታት በኋላ የኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ይነጋገራል meets አጀንዳዎቹም ዓለም አቀፍ ድንበሮችን መክፈትና የሕፃናት ክትባቶችን የሚመለከት ነው። 

የእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሳምባና ሞት በእጥፍ ተጋላጭ የሚያደርግ ጂን አገኙ። ጂኑ የደቡብ እስያ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ዘንድ በዝቶ የሚታይ ነው።

የኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,343 ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ፤ 10 ለሕልፈተ ሕይወት ተዳረጉ።

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 249 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 መያዛቸውንና ሶስት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አስመዘገበች።

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 

 

 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service