የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ቪክቶሪያ የጤና ሥርዓቷ ማሳሰቢያ የነበረውን የኮድ ቡናማ ማስጠንቀቂያዋን አነሳች

*** ከአንድ አሠት ዓመት ወዲህ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነርሶች ማክሰኞ ጠዋት ከ 7am ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ።

COVID-19 update

Nurse preparing a COVID-19 vaccine. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ እና ኩዊንስላንድን አካትቶ ባለፉት 24 ሰዓታት የ22 ሰዎች ሕይወት በኮቪድ 19 ሳቢያ አልፏል። ይህም ከወር ከፍ ባለ ጊዜ ውስጥ ዝቅተኛው የሞት ቁጥር ነው። 

  • ቪክቶሪያ ከሶስት ሳምንታት በኋላ የጤና ሥርዓቷ ማሳሰቢያ የነበረውን የኮድ ቡናማ ማስጠንቀቂያዋን አነሳች። ግብር ላይ ውሎ የነበረው የኦሚክሮን ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ወርኃ ጃኑዋሪ ውስጥ ነበር። 

  • የቪክቶሪያ ክፍለ አገር የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ ከዕለተ ዓርብ ጀምሮ የቡናማ ኮድ ማስጠንቀቂያ እንደሚያከትም በመንግሥት በኩል ሙሉ እምነት መኖሩን ጠቁመው፤ ሆኖም ሆስፒታሎች "በጣም በጣም ጥድፊያ የሚበዛባቸው" ሆነው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። 

  • በአሁኑ ወቅት 465 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምንና እየተከታተሉ ሲሆን፤ ጃኑዋሪ 17 ከተመዘገበው ከፍተኛው 1,229 የኮቪድ  - 19 ሕሙማን ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛው ነው። 

  • በቪክቶሪያ ጤና ዲፓርትመንት ዳታ መሠረት ክትባት ያልተከተቡ ሰዎች በኮቪድ ሲጠቁ ለፅኑ ሕሙማን ክፍል መዳረግ ሶስተኛ ዙር ክትባት ከተከተቡት ጋር ሲነፃፃር 34 እጅ እጥፍ ነው። 

  • የኩዊንስላንድ ጤና ሚኒስትር ኢቬት ዳት ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ የመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ መጠነ ሰፊ የቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አለመመዝገቡን ገለጡ። 

  • የኩዊንስላንድ መንግሥት የኮቪድ -19 አዲስ ተጠቂዎች፣ የሆስፒታል ሕሙማንና የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መሔዱን ከቀጠለ ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚገታ አስተወቀ። 

  •  ከአንድ አሠት ዓመት ወዲህ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነርሶች ነገ ማክሰኞ ጠዋት ከ 7am ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ። 

  • በዕለቱም አንድ ነርስ መከባከብ የሚችለው የበሽተኛ ቁጥር መጠን በአግባቡ እንዲሻሻልና የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ጥሪያቸውን ዳግም ያሰማሉ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 6,184 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ሆስፒታል ከሚገኙት 1,649 ሕመማን 100 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 7,104  በቫይረስ ሲጠቁ፤ 2 ሕይወታቸውን አጥተዋል።  ሆስፒታል ከሚገኙት 465 ሕመማን በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች 18 በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ። 

ኩዊንስላንድ 3,750 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 6 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 514 ሕመማን 41 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ታዝማኒያ 408 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 12 ሕሙማን መካክል አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 375 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። 

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

NSW 
ACT 
 

 






Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service