የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮቪድ-19 ተይዘው ዩናትድ ስቴትስ ውስጥ ወሸባ ገቡ

*** ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የቴኒስ ኮከቡ ኖቫክ ጆኮቪች አውስትራሊያ ኦፕን ላይ ተገኝቶ ለመጫወት 'እንደ ማንኛውም ሰው' የክትባት ደንቦችን ማክበር እንዳለበት ገለጡ።

Deputy Prime Minister Barnaby Joyce

Deputy Prime Minister Barnaby Joyce has tested positive for COVID-19 on his US tour. Source: AAP

  • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። የጤናቸው ሁኔታ ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ እስከሚያስችላቸው ድረስ እዚያው ወሸባ ገብተው ይቆያሉ።
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ደረሰ።
COVID-19 update
Source: S.Morrison
  • ኩዊንስላንድ እና ቪክቶሪያ ውስጥ በኦሚክሮን ቫይረስ የተያዙ የመጀመሪያ ሰዎች በተገኙበት ማግስት፤ የጤና ተጠባቢዎች ቫይረሱ አውስትራሊያ ውስጥ ከፍ ያለ ጫና እንደሚያሳድር አሳሰቡ። 
  • ሲድኒ ውስጥ በአንድ መጠጥ ቤት በተካሄደ የምሽት ዝግጅት ላይ የተገኙ 44 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ሆኖም ግለሰቦቹ የተጠቁት በአዲሱ ኦሚክሮን መሆን አለመሆኑ አልተገለጠም።
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ስምንት ሰዎች በኦሚክሮን ተያዙ፤ ክፍለ አገሪቱ ውስጥ በድምሩ 42 ሰዎች በአዲሱ ቫይረስ ተጠቅተዋል። 
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የቴኒስ ኮከቡ ኖቫክ ጆኮቪች አውስትራሊያ ኦፕን ላይ ተገኝቶ ለመጫወት  'እንደ ማንኛውም ሰው' የክትባት ደንቦችን ማክበር እንዳለበት ገለጡ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,232 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 420 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአንድ ግለሰብ ሕይወት አልፏል። 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አራት ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።  

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


 

 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service