የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ 'በእጅጉ አሳሳቢ' የኒው ሳውዝ ዌይልስ ገደቦች ጠበቁ

***ኒው ሳውዝ ዌይልስ 466 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ

COVID-19 update

NSW Police Force. Source: Getty

  • ኔው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ናረ
  • ሜልበርን ውስጥ የኮቪድ-19 ተጋላጭነት ሥፍራዎች ከ450 በላይ ደረሱ
  • ኩዊንስላንድ የማኅበረሰብ ተጋቦት አልባ ሆና አደረች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሰባት ደረሱ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 466 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ 68 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ገደብ ድንጋጌን ከፖሊስ ጋር ከሰኞ 16 ጀምሮ በጋራ ለማስከበር 500 የአውስትራሊያ መከላከያ አባላት መታከላቸውን እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን አስታወቁ። 

ከሲድኒ ወጥተው መጓዝ የሚፈልጉ የመዘዋወሪያ ፈቃድ ለማግኘት የማመልከት ግዴታ አለባቸው apply for a permit. ለሁሉም የሲድኒ ነዋሪዎች ከቤታቸው ወጥተው የመንቀሳቀስ ገደብ ከ10 ኪሎ ሜትር ወደ 5 ኪሎ ሜትር ዝቅ አለ።

ከሰኞ ኦገስት 16 ጀምሮ በ12 የአካባቢ መንግሥት ነዋሪዎች 12 local government areas of concern ከቤታቸው መውጣት የሚችሉት ለአካላዊ እንቅስቃሴና ልጆችን ለመከባከብ ሲሆን፤ ከቤት ውጪ ላለ መዝናኛ የተፈቀደ አይደለም። ለብቻቸው የሚኖሩ ላጤዎች ከወዲሁ የላጤ ወዳጃቸውን ሊያስመዘግቡ ይገባል nsw.gov.au.

የሕዝብ ጤና ትዕዛዞችን በሚጥሱ ሰዎች ላይ የሚጣለው ቅጣት ወደ $5,000 ከፍ ብሏል።

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 21 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ሶስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። አሥሩ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

የሜልበርን ቻድስተን የገበያ ማዕከል በኮቪድ-19 ተጋላጭነት ሥፍራ ተመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት ሜልበርን ውስጥ ሃይፖይንት የገበያ ማዕከልንና በርካታ አፓርትመንቶችን ጨምሮ ከ450 በላይ የተጋላጭነት ሥፍራዎች አሉ exposure sites in Melbourne

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination centres

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ስድስት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተውባታል። ሁሉም ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎችና ወሸባ ገብተው የነበሩ ናቸው። 
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አንድ ሰው በቫይረስ የተያዘባት ሲሆን በጠቅላላው ሰባት ሰዎች ተጠቅተዋል። 
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 

Share

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service