የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኦሚክሮን ቫይረስ አውስትራሊያ መዝለቅን ተከትሎ መንግሥት የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ 150 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ሶስቱ በአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሳይጠቁ እንዳልቀረ ተገምቷል።

COVID-19 update

Travelers look at a flight information notice board at Cape Town International Airport as restrictions on international flights take effect 28 Nov 2021. Source: AAP

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አመሻሽ ላይ የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ውይይትን ተከትሎ አውስትራሊያ የዘለቀውን አዲሱና በጣሙን ተዛማች የሆነው ኦሚክሮን ቫይረስ በቀጣዮቹ 48 ሰዓታት የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎች አስመልክቶ ክለሳ ለማድረግ የፀጥታ ስብሰባ ያካሂዳሉ። 

ከደቡብ አፍሪካ ወደ አውስትራሊያ የገቡ ሁለት መንገደኞች በአዲሱ ቫይረስ ተይዘው ተገኝተዋል። የአውስትራሊያ ዜግነት የሌላቸው ዘጠኝ የደቡባዊ አፍሪካ አገራት መንገደኞች ወደ አውስትራሊያ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የፌዴራል መንግሥቱ የሕክምና ባለሙያዎችን ምክረ ሃሳቦች አድምጦ እንደ አስፈላጊነቱ በጉዞ እገዳዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል። አውስትራሊያ ከረቡዕ ዲሲምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች፣ ባለሙያ ሠራተኞችና ባለቪዛዎች ድንበሮቿን ክፍት አድርጋለች።

በተጨማሪም መንግሥት የአውስትራሊያ ክትባት አማካሪ ቡድን ከአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሶስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት መከተቢያ ጊዜን እንዲከልስ በመንግሥት በኩል ጥያቄ ቀርቧል። በአሁኑ ወቅት ሶስተኛ ዙር የማጠንከሪያ ክትባትን ለመወጋት ሁለተኛ ዙር ክትባት ከተከተቡ በኋላ ለስድስት ወራት መጠበቅን ግድ ይላል።  

የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮንን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ በ Arabic | Simplified Chinese French | Russian | Spanish | Portuguese አውጥቷል።

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,007 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 150 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ሶስቱ በአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሳይጠቁ እንዳልቀረ ተገምቷል። 

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


 

 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service