የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑዕ ሕመምተኞች ቁጥር እየናረ ነው

*** በአገር አቀፍ ደረጃ 59 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል

COVID-19 update

Principal Glenn Butler takes delivery of Rapid Antigen Tests (COVID 19 Self Tests) at Mount View Primary School in Glen Waverley, Melbourne. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑዕ ሕመምተኞች ቁጥር እየናረ ነው።
  • ዛሬ በሚካሔደው ብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ላይ የተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ፣ ክተባና አቅርቦቶች ጉዳይ ይመከራል ተብሎ ይጠበቃል።
  •  33.4 ፐርሰንት ያህል ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ያሉ ልጆች የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ ክትባት ተከትበዋል።
  • የሶስተኛ ዙር ክትባት ቀነ ቀጠሮዎችን አስይዘው የሚቀሩ ነዋሪዎችን አስመልክቶ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ማሳሰቢያ ሰጡ።
  • የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ የሙሉ ክትባት ደረጃን ዕውን ማድረግ እንዲያስችል ብሔራዊ ካቢኔው የሶስተኛ ዙር ክትባት ከተባን ከግዴታ ጋር ሊያይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ። 
  • በአገር አቀፍ ደረጃ 59 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን አጡ።
  • 23 የሮያል አውስትራሊያ ባሕር ኃይል አደላይድ የጦር መርከበኞች በኮቪድ 19 መያዝ ጋር ተያይዞ ለቶንጋ 'ንኪኪ አልባ' የእርዳታ አቅርቦት ተደረገ።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤ 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 17,316  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ29 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,722 ሕመማን 181ዱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 13,755 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 15 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  ሆስፒታል ከሚገኙት 1,057 ሕመማን 117ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

 ኩዊንስላንድ 11,600 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 15 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 829 ሕመማን 48 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ደቡብ አውስትራሊያ  1,953 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 288 ሕመማን 27 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የሆስፒታል ሕሙማን 73 ሲደርስ አራት በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

NSW 
ACT 
 





 

Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑዕ ሕመምተኞች ቁጥር እየናረ ነው | SBS Amharic