የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ 'የክትባት መጠን 80 ፐርሰንት ሲደርስ ሕይወት የተሻለ ይሆናል' እያለች ነው

*** ቪክቶሪያ ተጋላጭ ለሆኑ ማኅበረሰባትከ 20 ሚሊየን ዶላርስ በላይ የድጋፍ እቅዷን አስታወቀች

COVID-19 update

Members of the Indigenous community are seen receiving a Covid-19 vaccine at a pop-up vaccination clinic at the National Centre of Indigenous Excellence. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 40 ፐርሰንት ነዋሪዎች የሁለተኛ ዙር ክትባት ተከትበዋል
  • ቪክቶሪያ ተጋላጭ ለሆኑ ማኅበረሰባት የድጋፍ እቅዷን አስታወቀች
  • 15 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቁ
  • ኩዊንስላንድ አንድ ሰው በቫይረስ የተያዘባት መሆኑን አስመዘገበች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,485 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከአንድ ሺህ በላይ ሕሙማን ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ፤ 175ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ውስጥ ሲገኙ 72ቱ የመተፈንሻ ቁሶች ተገጥሞላቸዋል።

ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ውስጥ 40 ፐርሰንቱ የሁለተኛ ዙር 73 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል። እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች የክትባት ደረጃ 80 ፐርሰንት ሲደርስ ኒው ሳውዝ ዌይልስ  "ዳግም ክፍለ አገር  አቀፍ ገደቦች አይጣልባትም" ብለዋል። ሆኖም በሚቀጥሉት አሥራ አራት ቀናት በቫይረስ የሚጠቁ ሰዎች ቁትር እንደሚያሻቅብ አስጠንቅቀዋል። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 183 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 110ሩ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። 

ሚኒስትር ሉክ ዶኔላን ተጋላጭ ለሆኑ ማኅበረሰባት መርጃ የሚውል የ$27 ሚሊየን ድጎማ መመደቡን ይፋ አድርገዋል support package 

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 15 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ 13ቱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። ስድስቱ በወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ አንዲት እናት በቫይረስ ተዛለች፤ ልጇ በትናትናው ዕለት በቫይረስ ተጠቅቶ ነበር።
  • የምዕራብ አውስራሊያ እንደራሴ የክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ ነዋሪዎች የክትባት መጠን 80 ፐርሰንት ሳይደርስ የክፍለ አገሩ ወሰን ክፍት የሚሆንበት ቀን እንደማያስታውቁ ገለጡ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 


Share

Published

Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ 'የክትባት መጠን 80 ፐርሰንት ሲደርስ ሕይወት የተሻለ ይሆናል' እያለች ነው | SBS Amharic