የሜልበርን የፈረስ እሽቅድድም ዋንጫን ለመመልከት 10,000 ተመልካቾች ሊታደሙ ነው

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ከነገ ጀምሮ ሊረግቡ ነው

COVID-19 update

Source: AAP

  • የሜልበርን ዋንጫ ላይ 10,000 ሙሉ ክትባት የተከተቡ ታዳሚዎች እንዲገኙ ተፈቀደ 
  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ገደቦች በነገው ዕለት ሊረግቡ ባለበት ዋዜማ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር 90 ፐርሰንት ደረሰ
  • በአንዲት በቫይረስ የተጠቃች የቨርጂን አየር መንገድ አስተናጋጅ ሳቢያ የሶስት ክፍለ አገራት ጤና ባለ ስልጣናት በተጠንቀቅ ናቸው  


ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,890 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የአምስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተከታተሉ ካሉ ሕሙማን ውስጥ ከ 7 ፐርሰንት ያነሱቱ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ናቸው።
ቪክቶሪያ ውስጥ ንኪኪ አላቸው የተባሉ ግለሰቦች ሁሉ ላይ ከማተኮር ይልቅ በቫይረስ የተያዙና ዋነኛ ቅርብ ንኪኪ ያላቸው ላይ ማተኮር ተጀምሯል።  

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ የክትባት መጠኑ 80 ፐርሰንት ሲደርስ የክፍለ አገሩ ምጣኔ ሃብት እንደምን ሊንቀሳቀስ እንደሚችል ሙከራዎችን ለማካሄድ በርካታ ኩነቶች አንዱ የሙከራ አካል እንደሚሆን ጠቆሙ። 

ሜልበርን ኦክቶበር 30 ላይ 'ጥቂት ሺህዎች ታዳሚዎች' የሚገኙበት የመድረክ የሙዚቃ ዝግጅት ታካሂዳለች።

የሜልበርን ዋንጫም ኖቬምበር 2 ሙሉ ክትባት የተከተቡ 10,000 ታዳሚዎች ይገኛሉ።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 477 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ነዋሪዎች ውስጥ 90 ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል።  

72.8 ፐርሰንት ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከትበዋል። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ቁሻሻ ፍሳሽ ፕሮግራም ሃንተር ኒው ኢንግላንድ ሪጅን ኡራላ ውስጥ የቫይረስ ናሙናዎችን አግኝቷል።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ኩዊንስላንድ አንድም ነዋሪ በኮቪድ-19 አልተያዘባትም።
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 30 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 16 ተያያዥነት ያላቸው ሲሆኑ የተቀሩት ምርጫቸው በምርመራ ላይ ይገኛል።
  • አንዲት በቫይረስ የተጠቃች የቨርጂን አየር መንገድ አስተናጋጅ ከ ኦክቶበር 4 እስከ 6 በሜልበርንና አደላይድ፤ ሲድኒና ኒው ካስትል መካክለ መሥራት የሶስት ከፍለ አገራት ጤና ባለ ስልጣናትን አሳስቧል።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 

 





 
 

 

Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service