የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይል በፈረንጆች ገና ዓለም አቀፍ ድንበሯን ለመክፈት ወጥናለች

*** ቪክቶሪያ ውስጥ በመጪው ሳምንት 7,000 የመጀመሪያ ዙር ፋይዘር ከትባት ቀጠሮዎች ለተከታቢዎች ክፍት ይሆናሉ

COVID-19 update

A return traveler prepares to board a quarantine bus at Sydney International Airport, Wednesday, September 8, 2021. Source: AAP

  • ከነገ ጀምሮ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የተወሰኑ ገደቮች ይረግባሉ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ 7,000 የፋይዘር ከትባት ቀጠሮዎች ክፍት ሆነው ተከታቢዎችን እየጠበቁ ነው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 15 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲጠቁ ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ሰው በቫይረስ አልተያዘም

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,262 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ከሰኞ ሴፕቴምበር 13 ጀምሮ በ12ቱ የስጋት አካባቢ መንግሥት ነዋሪዎችን ስያካትት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ከአምስት ያልበለጡ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ 12 local government areas (LGAs) of concern በ12ቱ የስጋት አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑና ሙሉ ክትባት የተከተቡ አብረዋቸው በአንድ ቤት ከሚኖሩ የቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር በመሆን በቀን ለሁለት ሰዓታት ለሽርሽር ወይም ለመዝናናት እንዲሁም ላልተወሰነ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከቤታቸው መውጣት ይችላሉ። 

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ የመጀመሪያ ዙር ተከታቢዎች ቁጥር 78 ፐርሰንት፣ ሙሉ ክትባት የተከተቡቱ 45.58 ሲደርስ ዓለም አቀፍ ድንበሮቿን ለመክፈት መወጠኗን አስታወቁ።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 334 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ በመጪው ሳምንት 7,000 የመጀመሪያ ዙር ፋይዘር ክትባት በመንግሥት ስር ባሉ ክሊኒኮች ለተከታቢዎች እንደሚዳረሱ አስታወቁ።

ቪክቶሪያ ውስጥ በስምንት ትምህርት ቤቶችና የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ሂዩም፣ ዳንዲኖንግ እና ካሲ፤ እንዲሁም ቶርንበሪ የሚገኘውን የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ሚል ፓርክ የሚገኘውን የሂንዱ መቅደስና ኒውፖርት የሚገኘውን መስጊድ ጨምሮ አዲስ የክትባት መከተቢያዎች ይከፈታሉ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre                                                                                                       

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አንድ ሚሊየን ተጨማሪ የሞደርና ኮቪድ-19 ክትባት ለማናቸውም ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ በክትባትነት እንዲሰጥ ይሁንታ መቸሩን ገለጡ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 

 


Share

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service