የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከኦክቶብር ጀምሮ የትምህርት ቤት መማሪያ ክፍሎችን ለተማሪዎች ልትከፍት ነው

*** የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ፋይዘር ክትባት እንዲከተከቡ ይሁንታውን ቸረ

COVID-19 update

Thousands of Year 12 HSC students got their Pfizer vaccinations at the Mass Vaccination hub at Qudos Arena in Sydney, Monday, August 9, 2021. Source: AAP

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እስከ ኖቬምበር 9 ተራዘመ
  • ከ10 አንድ በቫይረስ የተጠቁ ቪክቶሪያን የሚገኙት ሼፐርተን ውስጥ ነው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ ገደቦችን ከለሰች
  • የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ፋይዘር ክትባት እንዲከተከቡ ይሁንታውን ቸረ 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 882 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ብቫይረሱ ከተያሹት ውስጥ ከ80 ፐርሰንት በላይ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። በ60ዎቹና በ90ዎቹ ዕድሜ የነበሩ ሁለት ወንዶችም ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።  

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ዕቅዶችን ይፋ አድርገዋል።:

  • ከኦክቶበር 25 ጀምሮ - ከአጸደ ሕጻናት እስከ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች
  • ከኖቬምበር 1 ጀምሮ - የ 2ኛ፣ 6ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪዎች
  • ከኖቬምበር 8 ጀምሮ - የ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች
ከኖቬምበር 8 ጀምሮ ለሁሉም የትምህርት ቤት ባልደረቦች ከትባት መከተብ ግዴታ ሲሆን፤ ከሴፕቴምበር 6 ጀምሮ እንዲከተቡ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።  

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ያስይዙ vaccination appointment 


ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 79 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 53ቱ ቀደም ብለው ከሚታወቁ ሥፍራዎች ሲሆኑ 26 ምንጫቸው ያልታወቀ ናቸው።

ከ 65,000 የሸፐርተን ነዋሪዎች ውስጥ 16,000 ያህሉ ራሳቸውን አግልለው ለመቆየት ግድ በመሰኘታቸው ምግብ አከፋፋዮች፣ ትላልቅ ሱቆችና መድኃኒት ቤቶች በሠራተኞች እጥረት ሳቢያ ተዘግተዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 21 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 221 ደርሷል።

ብሔራዊ መዲናይቱ ለንግድና ግልጋሎት ሰጪዎች ያካሄደችው ማሻሻያ ከዛሬ 11.59pm ጅርምሮ ግብር ላይ ይውላል changes for retail business, waste drop-off services, gym and dance schools and real estate business 

የኮቪድ-19 ክትባት መሥፈርትን የሚያሟሉ ስለመሆንዎ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ከዛሬ 4pm ጀምሮ የደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ የኮሮናቫይረስ ገደቦች በተጨማሪ ይላላሉ COVID-19 restrictions 
  • የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ፋይዘር ክትባት እንዲከተከቡ ይሁንታውን ቸረ 
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 

Share

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service