የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ከ1000 በላይ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል፤ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ነዋሪዎች ተጨማሪ ነፃነቶች ታክለዋል

*** ቪክቶሪያ 80 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።

COVID-19 update

Members of the public wear face masks as they exercise in Sydney, Thursday, August 26, 2021. Source: AAP

  • የሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ኮሮናቫይረስ ገደብ እስከ ሴፕቴምበር 10 ተራዘመ
  • ቪክቶሪያ 25,000 የፋይዘር ክትባቶችን ተቀበለች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶር የንግድ ድጎማ ተጀመረ
  • ኩዊንስላንድ ቱዉምባ አጠገብ የወሸባ ማዕከል ልትገነባ ነው

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,029 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 37 በማኅበረሰብ ውስጥ የተዛመቱ ናቸው። የሶስት ክትባት ያልተከተቡ ሰዎች ሕይወትም አልፏል። 

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ሙሉ ክትባት ለተክተቡ ነዋሪዎች ከሴፕቴምበር 13 ጀምሮ ተጨማሪ ነፃነቶችን አስታውቀዋል፤ 

  • የስጋት ሥፍራዎች ከሆኑ የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ውጪ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ከቤታቸው አምስት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውስጥ ባሉ ሥፍራዎች ከአምስት ሳይበልጡ መሰባሰብ ይችላሉ
  • የስጋት አካባቢ በሆኑ የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ነዋሪ የሆኑ ቤተሰቦችም ከቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ፤ ሆኖም የሰዓት ዕላፊና የአካል እንቅስቃሴን አስመልክቶ ያሉ ገደቦችን ማክበር ይጠበቅባቸዋል local government areas of concern .
ዛሬውኑ የክትባትዎን ቀጠሮዎን ያስይዙ vaccination appointment.

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 80 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 41ዱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

የቪክቶሪያን  25,000 ክትባቶች መቀበል ተከትሎ የኮቪድ ኮማንደር ጄሮን ዌይማር እንዳስታወቁት ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች ሆኖ የአስትራዜኔካ ክትባት ቀጠሮ ያላቸው በቀጥታ ያለ ተለዋጭ ቀጠሮ የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ይችላሉ።

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 


የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 14 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 190 ደርሷል።

ንግዳቸው በተጣለ ገደብ የተጎዳባቸውና ሠራተኞችን ቀጥረው የሚያሠሩ የካንብራ ኩባንያዎች እስከ $10,000 ያለ ተቀጣሪ ያሉ ነጋዴዎች እስከ  $4,000 ድጎማ ማመልከት ይችላሉ apply for grants 

የኮቪድ-19 ክትባት መሥፈርትን የሚያሟሉ ስለመሆንዎ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ቱዉምባ ዌልካምፕ አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ሪጂናል የወሸባ ማዕከል ልትገነባ ነው
  • ኖርዘርን ቴሪቶሪ የሚገኙ ማናቸውም ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባቶችን መከተብ ይችላሉ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 

Share

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ከ1000 በላይ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል፤ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ነዋሪዎች ተጨማሪ ነፃነቶች ታክለዋል | SBS Amharic