የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይል የመከላከያ ሠራዊት አባላትን አሰማራች፤ ኩዊንስላንድ ገደቧን አራዘመች

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 207 በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ስዎችን አስመዝግባለች፤ ኩዊንስላንድ ውስጥ በቫይረሱ ከተጠቁት ውስጥ አብዛኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ናቸው።

COVID-19 update

Australian Defence Force personnel and NSW police are seen being deployed from Fairfield Police Station in Sydney, Monday, August 2, 2021. Source: AAP

  • በኒው ሳውዝ ዌይልስ አሁንም ድረስ በማኅበረሰብ ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ከፍተኛ ነው
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ በአብዛኛው በቫይረሱ የተያዙት ልጆች ናቸው
  • ቪክቶሪያ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል
  • ደቡብ አውስትራሊያ ተጥለው የነበሩ የተወሰኑ ገደቦች ተነሱ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 207 በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ስዎችን አስመዝግባለች። በቫይረሱ ከተያዙት ውስት 50ዎቹ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። አንድ በ90ዎቹ ዕድሜ ያሉና የመጀመሪያ ዙር አስትራዜኒካ ኮቪድ -19 ክትባት የተከተቡ አረጋዊ ሕይወትም ሊቨርፑል ሆስፒታል ውስጥ አልፏል።  

300 ያህል የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል አባላት "እሽግ ምግቦችን በማደል፣ ለረድኤት ግልጋሎት በሮችን በማንኳኳትና የድንጋጌ አፈጻጻምን በመቆጣጠር" ረገድ በስምንት አካባቢዎች eight local government areas እገዛ ማድረግ ጀምረዋል። የጦር ሠራዊት አባላቱ የታጠቁ አይደሉም።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ነዋሪዎች ከትባት እንዲከተቡ እያበረታቱ ነው። የክትባት መስጫ ክሊኒኮችን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት 13 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት መሆኗን አስታወቀች። በቫይረሱ ከተጠቁት ውስጥ አብዛኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። ሁሉም በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቫይረሱ ተስፋፍቶባቸው ያሉ አካባቢዎች ነዋሪዎች ናቸው። በጠቅላላው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 31 ደርሷል። 

በጅሮንድ ካሜሮን ዲክ በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች እገዛ እንደሚያገኙ አስታውቀዋል $260 million package to support Queensland businesses

ተጥሎ ያለው ገደብ በ Brisbane, the Gold Coast, Ipswich, Lockyer Valley, Logan, Moreton Bay, Noosa, Redland, Scenic Rim, Somerset and the Sunshine Coast እስከ እሑድ ኦገስት 8 ተራዝሟል። 

ቫይረስ የተስፋፋባቸውን አካባቢዎች ለማወቅ ይህን ይጫኑ list of exposure sites.

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሁሉም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው

  • ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግዴታ ሆኖ ሲቀጥል፤ የተወሰኑ ተመልካቾችን ያካተቱ የስፖርት ውድድሮች እንዲካሄዱ ተፈቅዷል።
 


ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 

Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይል የመከላከያ ሠራዊት አባላትን አሰማራች፤ ኩዊንስላንድ ገደቧን አራዘመች | SBS Amharic