- ቪክቶሪያ ውስጥ በቅርቡ በቫይረስ ከተያዙት 45 ፐርሰንቱ ዕድሜያቸው ከ30 በታች ነው
- ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌልስ ሊዝሞር ላይ የተጣለው የሰባት ቀናት ገደብ ዛሬ ይጀምራል
- ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ የካንብራ ነዋሪዎች ውስጥ ከ93 ፐርሰንት በላይ ተከትበዋል
- ኩዊንስላንድ አንድ ነዋሪዋ በቫይረስ መያዙን አስመዘገበች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,377 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የአራት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
የሚልዱራ ቁሻሻ ፍሰት ውስጥ ቫይረስ ተከስቶ ተገኝቷል። የሪጂናል ቪክቶሪያን ሞርዌል እና ሼፐርተንን አክሎ ተጨማሪ የመጀመሪያ ደረጃ ተጋላጭነት ሥፍራዎች ተመዘገቡ
የሜልበርን ነዋሪዎች በስድስት ገደቦች ውስጥ 246 ቀናትን በማሳለፍ የአርጀንቲናን መዲና ቦይኖስ አይረስን የገደብ ሬኮርድ አልፈዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 623 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ሊዝሞር ላይ እስከ ኦክቶበር 11 ፀንቶ የሚቆይ ገደብ ተጣለ። ከሴፕቴምበር 28 ጀምሮ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችንም ይጨምራል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ ገደቦቿን ለማርገብ የመጨረሻው ሳምንት ላይ በምትገኝበት ወቅት ኦክቶበር 2 ዕኩለ ለሊት ላይ ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 67.1 ደርሷል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ቴሪቶሪ ካፒታል ውስጥ 28 ሰዎች በቫይረስ ሲያዙ ሁለት ነዋሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት 16 የኮቪድ ሕሙማን ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አምስቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል አንድ በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
የክትባት መመዘኛን ከሚያሟሉ ነዋሪዎች ውስጥ 93 ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የኩዊንስላንድ ተጋላጭነት ሥፍራዎች ቁጥር ጨምሯል exposure list አንድ ግለሰብ በቫይረስ ተጠቅቶ ለ10 ቀናት በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲዘዋወር ነበር
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤