- ቪክቶሪያ የተከታቢዎችን መጠን ከፍ ለማድረግ $21 ሚሊየን ዶላርስ መደበች
- በሪጂናል አውስትራሊያ የቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ሆኗል
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ገደቦቿን አረገበች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,749 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ 89.4 ፐርሰንት የቪክቶሪያ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት ሲከተቡ 67.2 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ተጨማሪ ተንቀሳቃሽ የክትባት ክሊኒኮችን፣ የክትባት ቀጠሮ ማስያዣዎችን፣ ትራንስፖርትና አሥፈላጊ ለሆኑ አማራጭ የማኅበረሰብ ፍላጎት ማሟያዎችን አካትቶ የተከታቢዎችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ተግባር ላይ የሚውል $21 ሚሊየን ዶላርስ መመደቡን ገለጡ።
የቪክቶሪያ መንግሥት የሙሉ ክትባት ተከተባዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት ላይ ሲደርስ የወሸባ ቀናት ድንጋጌዎች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ግብር ላይ እንደሚውሉ አረጋግጧል።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 273 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ዕድሚያቸው ከ12 እስከ 15 ካሉ ልጆች ውጥ 75 ፐርሰንት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ሲሆን 35.5 ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
እንዲሁም ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ነዋሪዎች ውስጥ ከ80 ፐርሰንት በላይ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት የቫይረሱ ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ መስፋፋት አስጊ በመሆኑ ነዋሪዎች እንዲከተቡ አሳስበዋል።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 24 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 21ዱ የቫይረሱ መስፋፋት ከታወቀባቸው ሥፍራዎች ናቸው።
ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት ተከታቢዎች ቁጥር 80 በመድረሱ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ረግበዋል።
ሁሉም አስፈላጊነታቸው ከፍ ያለና ውስን የሆኑ የችርቻሮ ግልጋሎት ሰጪዎች በሙሉ ከሐሙስ ኦክቶበር 21 11:59pm ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ።
ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ የሙሉ ክትባት ተከታቢዎቿ መጠን 70% ፣ 80 እና 90% ፐርሰንት ሲደርስ ለአገር ውስጥ ዓለም አቀፍ መንገደኞች የነደፈችውን ዕቅድ ይፋ አደረገች unveiled plans
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

