የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ ከአሁኑ የከፋ የቫይረስ መስፋፋት እንደሚከስት አስጠነቀቁ

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,431 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና 12 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት መዳረጋቸውን አስታወቀች

COVID-19 update

People are seen exercising outdoor at Parramatta park in Sydney, Friday, September 3, 2021. Source: AAP

  • 1,000 የኒው ሳውዝ ዌይልስ ኮቪድ ሕሙማን ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ 50,000 የአስትራዜኔካ ክትባትን መከተብ ለሚሹ ዝግጁ ነው
  • በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ክፍያ ላስተጓጎሉ ተከራዮችን ጥበቃ የአሥራ ሁለት ሳምንት ድንጋጌ አለፈ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,431 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የዴልታ ቀውስ በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ይበልጡን እንደሚስፋፋ አመላከቱ።

በአሁኑ ወቅት 979 የኮቪድ-19 ሕሙማን ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ከእነሱም ውስጥ 160 ፅኑዕ ሕሙማን ክፍል 63 የአየር መተንፈሻ ተገጥሞላቸው ይገኛሉ። የጤና ባለ ስልጣናት በሚቀጥሉት አሥራ አራት ቀናት የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥር እንደሚጨምር ከወዲሁ አሳስበዋል።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 208 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 96ቱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። የአንድ በ60ዎቹ የሚገኝ ግለሰብ ሕይወት አልፏል።  

እንደራሴ አንድሩስ ከማክሰኞ ሴፕቴምበር 7 ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቅድሚያ ተሰጧቸው ክትባት መከተብ እንደሚጀምሩና በቀጣይነትም ዕድሚያቸው 12 ላለ ልጆች የፋይዘር  ኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 18 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ 15ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

መንግሥት በገደቦች የተነሳ ገቢያቸውን በማጣት ወይም የሥራ ሰዓታቸው በመቀነሱ ሳቢያ የቤት ኪራያቸውን መክፈል ለተሳናቸው ለአሥራ ሁለት ሳምንታት ኪራያቸው ተቋርጦ ከኪራይ ቤታቸው እንዲወጡ እንዳይደረግ ድንጋጌ አሳለፈ a twelve-week moratorium on evictions for rent 

የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccination 

ያእፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ከሰኞ ሴፕቴምበር 6 አንስቶ ኩዊንስላንድ ውስጥ 680 የሆቴል ወሸባ ክፍሎች ስንዱ ይሆናሉ  
  • ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ቡድናት ውስጥ አንዱ ቢሆኑም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ ነባር ዜጎች እስካሁን መከተብ የቻሉት 20 ፐርሰንት ብቻ ናቸው
  • ተጠባባቂ እንደራሴ ጀርሚ ሮክሊፍ ታዝማኒያ ውስጥ የሚገኙ የጤና ክብካቤ ሠራተኞች ላይ ክትባት የመከተብ ግዴታ መጣሉን አስታወቁ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 

 


Share

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service