የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከ1,000 በላይ ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ መጠቃታቸውን አስታወቀች

*** ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ሊራዘም ነው

COVID-19 update

Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ፈቃድ ላላቸው ሠራተኞች አዲስ የክትባት መስፈርቶች ወጡ
  • ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ሊራዘም ነው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 13 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ
  • ኩዊንስላንድ አንድ የቤት ውስጥ ወሸባ ገብቶ ያለ ግለሰብ በቫይረስ መያዙን አስታወቀች 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,218 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 887ቱ ፐርሰንት በላይ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በጠቅላላው ከኮቪድ ጋር በተያያዘ 145 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።   

ከሰኞ ሴፕቴምበር 6 ጀምሮ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች የሆኑ ሠራተኞች ከቀዬአቸው ዉጪ ተጉዘው ለመሥራት ቢያንስ የአንድ ዙር ክትባት የመከተብ ግዴታ ይኖርባቸዋል local government areas of concern 

የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች የሆኑ ሠራተኞች፣ ዕድሜያቸው ከ16- 19 ሆኖ ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ለሆኑና ነዋሪነታቸው ወይም የሥራ ገበታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ሆኖ በሕፃናት ክብካቤ፣ የግብረ አካል ጉዳተኞችና የምግብ ሠራተኞች ዘርፍ ለሆኑ የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል authorised workers who live in a LGA of concern,  people aged 16-49 who live in a LGA of concern and childcare, disability and food workers who live or work in a LGA of concern.  

የኮቪድ-19  ከትባት ማረጋጋጫ እንደምን ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ how to get proof of your COVID-19 vaccinations.

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 92 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 30ዎቹ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ሥፍራዎች አይደሉም።

በጠቅላላው በቫይረሱ ከተያዙት 778 ሰዎች ውስጥ 500 ያህሉ የሰሜንና ምዕራብ ነዋሪዎች መሆናቸውን እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ጠቁመው በታካይነትም ቀነ ገደቡ ሴፕቴምበር 2 የሚያበቃውን ገደብ ለማርገብ አዋኪ መሆኑን አስታውቀዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ከሴፕቴምበር 8 ጀምሮ ቡንዳል በሚገኘው የብሪስበን የመዝናኛ ማዕከል የመጠነ ሰፊ የክትባት ማዕከል ትከፍታለች
  • የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የ COVID-19 Vaccine Claim Scheme በ TGA የጸደቀውን ክትባት ለሚከተቡ  አውስትራሊያውያን ጥበቃ እንደሚቸራቸው ገለጡ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 

Share

Published

Updated

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከ1,000 በላይ ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ መጠቃታቸውን አስታወቀች | SBS Amharic