የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሌላ ከፍተኛ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሬኮርድ አስመዘገበች

***ቪክቶሪያ 45 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።

COVID-19 update

Members of the public exercise at Bondi Beach in Sydney, Wednesday, August 25, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዳግም አሻቀበ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ አብዛኛዎቹ በኮቪድ-19 የተጠቁት ወጣቶች ናቸው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የኮቪድ-19 ግብረ ኃይሏን አጠናከረች
  • ኩዊንስላንድ የሆቴል ወሸባ ፕሮግራሟን ገታች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 919 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታወቀች፤ 37 በማኅበረሰብ ውስጥ የተዛመቱ ናቸው። የሁለት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። 

Guildford, Auburn, Merrylands, Greystanes, Granville, Punchbowl, Yagoona እና Blacktown ስጋት ካለባቸው ክፍለ ከተማነት አልወጡም። 

ዋና የጤና መኮንን ኬሪ ቻንት የፅኑዕ ህሙማን ክፍሎች ውስጥ ከሚገኙ 113 ህመምተኞች ውስጥ 98ቱ ያልተከተቡ መሆናቸውን ገልጠዋል።

ዛሬውኑ የክትባትዎን ቀጠሮዎን ያሲይዙ vaccination appointment 

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 45 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 28ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ እንዳስታወቁት ከ538 በቨይረስ የተጠቁ ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በለይ የሆኑቱ ከ30ዎቹ በታች ያሉ ሲሆኑ 114 ዕድሜያቸው ከዘጠኝ ዓመት በታች ነው።

ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 17 የፋይዘር ክትባት መከተብ የሚችሉ ሲሆን ከ18-39 የሚገኙ ከአስትራዜኔካ ወይም ፋይዘር ከትባቶች አንዱን መርጠው መከተብ ይችላሉ። ዕድሜያቸው 60 እና ከዚያ በላይ ለሆኑት ግና አማራጩ ክትባት አስትራዜኔካ ብቻ ነው።

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 9 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 176 ደርሷል።

የጤና ሚኒስትር ራቼል ስቴፈን ነርሶች፣ ተማሪ ነርሶችና ተማሪ አዋላጆች ከታሳቢ የክትባት አቅርቦት ጭማሪ ጋር የክትባት ሂደቱም አብሮ እንዲሄድ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጠዋል።  

የኮቪድ-19 ክትባት መሥፈርትን የሚያሟሉ ስለመሆንዎ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.   

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • በሆቴል ወሸባ መጨናነቅ ሳቢያ ኩዊንስላንድ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ እና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ላይ እስከ ሴፕቴምበር 8 ድረስ እገዳ ጥላለች
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤



ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 

Share

Published

Updated

Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service