- ቪክቶሪያ ለከቤት ውጪ ንግድ የምጣቤ ሃብት መደጎሚያ እንደምትሰጥ አስታወቀች
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ
- ታዝማኒያ በነደፈችው ዕቅድ መሠረት ገደቦቿን ልታነሳ ነው
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,903 በቫይረስ ተጠቁ፤ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
የሥራ ሚኒስትር ጃላ ፑልፎርድ የአካል እንቅስቃሴ ማጠንከሪያ፣ ችርቻሮ፣ የውበት ሳሎንን ለመሳሰሉ ንግዶችና ድርጅቶች የከቤት ውጪ ንግድ መቋቋሚያ የሚሆን $54 ሚሊየን ዶላርስ የቪክቶሪያ መንግሥት መመደቡን አስታወቁ $54 million for businesses and organisations
ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከ89.2 ፐርሰንት በላይ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 66.5 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
ሐሙስ ኦክቶበር 21 ዕኩለ ለሊት ላይ ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ይረግባሉ። ዓርብ ኦክቶበር 22 ሁሉም ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 265 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ዘጠና ፐርሰንት ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሲሆን 80.3 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት ተከትበዋል።
በዛሬው ዕለትየ12ኛ ክፍል 1ኛ ክፍልና የሙዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ከሌሎች ቀደም ብለው ተመለስዋል። የተቀሩት ተማሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 17 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 11ዱ የቫይረሱ መስፋፋት ከታወቀባቸው ሥፍራዎች ናቸው።
ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ አንድም በቫይረስ የተያዘ ግለሰብ አላስመዘገበችም።
- ደቡብ ታዝማኒያና መዲናይቱ ሆባርት በተነደፈላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ዛሬ ምሽት 6pm ላይ የተጣሉባቸው የኮሮናቫይረስ ገደቦች ይነሱላቸዋል።

