- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ምንጫቸው ለጊዜው ባልተለየ ኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች አካባቢዎች ተከስተዋል
- ቪክቶሪያ ውስጥ ከ 70,000 በላይ አስትራዜኔካ ክትባቶች በመንግሥት ክሊኒኮች ውስጥ ለክትባት ዝግጁ ሆነው አሉ
- የአውስራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ የፋይዘር ክትባት ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 29 ላሉ የክትባት ቀጠሮ ክፍት ሆኗል
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,116 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በትሬድቦ ዌስትዎተር፣ ሜሪምቡላ፣ ፖርት ማኳየሪ፣ ዳንቦጋን፣ ቦኒ ሂልስ፣ ዋረን ሞሎንግ፣ ታምዎርዝ እና ጋኒዳህ አካባቢዎች ኮቪድ-19 ተከስቷል።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ዓለም አቀፍ ጉዞ በኖቬምበር እንደሚጀምር ፍንጭ ሰጥተዋል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment የኮቪድ-19 ክትባት ማረጋገጫዎን እንደምን ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ ይህን ይጫኑ how to get proof of your COVID-19 vaccination.
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 120 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የሁለት ሰዎች ሕይወት ለሕልፈት በቅቷል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ሴፕቴምበር 23 ላይ 70 ፐርሰንት መድረስ ከቻለ አሁን ተጥሎ ያለው የ5 ኪሎ ሜትር የጉዞ ገደብ ወደ 10 ኪሎ ሜትር ከፍ እንደሚል አስታውቀዋል easing of restrictions
የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ የኮንስትራክሽን ሠራተኞች ቁጥር 90 ፐርሰንት ሲደርስ የኮንስትራክሽን ሥራ በ50 ፐርሰንት መቀጠል ይችላል።
ከሴፕቴምበር 7 ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክትባት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይደረጋል። የጠቅላላ ስኬት ፈተና ኦክቶበር 5 የሚካሄድ ሲሆን በተርም 3 ተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተገኝተው መማር አይችሉም።
ከነገ እኩለ ለሊት ጀምሮ የመጫወቻ ሥፍራዎች ክፍት ይሆናሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 23 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ 12 ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 29 ያለ የካንብራ ነዋሪዎች በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ መንግሥት መጠነ ሰፊ ክሊንክ ወይም ተሳታፊ ጠቅላላ ሐኪም ዘንድ በመሄድ የፋይዘር ክትባት መከተብ ይችላሉ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤