የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኩዊንስላንድ ወሰኗን ሙሉ ክትባት ለተከተቡ የአገር ውስጥ ተጓዦች ከፈተች

*** ደቡብ አውስትራሊያ በሚቀጥለው ሳምንት እንደታሰበው ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎቿ ቁጥር 80 ፐርሰንት ከደረሰ በኋላ ገደቦችን እንደማትጥል አስታወቀች።

COVID-19 update

A Virgin Australia plane is seen on approach into Brisbane airport. Source: AAP

  • ከዛሬ ሰኞ 5pm አንስቶ ሙሉ ክትባት የተከተቡ፣ ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ነፃ የመሆናቸው ማረጋገጫ ያላቸው ለ14 ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ መግባት የሚፈቅዱ ሰዎች ወደ ኩዊንስላንድ በአየር መጓዝ ይችላሉ። ኩዊንስላንድበሯን ለጎብኚዎች የከፈተችው ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት በመድረሱ ነው። 

  • ደቡብ አውስትራሊያ በሚቀጥለው ሳምንት እንደታሰበው ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎቿ ቁጥር 80 ፐርሰንት ከደረሰ በኋላ ገደቦችን እንደማትጥል አስታወቀች። 

  • የቪክቶሪያ መንግሥት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እንዲያግዝ ፈጣን የመመርመሪያ ቁሶችን ለሙዋዕለ ሕፃናትና የረጅም ቀን የሕፃናት ክብካቤ ለሚሰጡ ማዕከላት በዚህ ሳምንት አከፋፈለ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 860 በቫይረስ ሲጠቁ፤ አምስት ሕይወታቸውን አጥተዋል።  
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 165 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አስታወቀች። 

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 





 
 

 

 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኩዊንስላንድ ወሰኗን ሙሉ ክትባት ለተከተቡ የአገር ውስጥ ተጓዦች ከፈተች | SBS Amharic