የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኩዊንስላንድ የ80 ፐርሰንት ኮቪድ- 19 ገደቦች ማርገቢያ ፍኖተ ካርታዋን ይፋ አደረገች

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 1,069 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ 10 ሕይወታቸውን አጥተዋል።

COVID-19 update

Kiongozi wa Queensland Annastacia Palaszczuk (katikati), akizungumza na wafanyakazi katika kituo cha chanjo cha Logan. Source: AAP

  • ኩዊንስላንድ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ነዋሪዎች የተለያዩ ገደብ ማርገቢያዎችን ይፋ አደረገች።
  • ከዲሴምበር 17 ወይም ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሲደርስ በመጠጥ ቤቶች፣ ሌሎች መዝናኛዎች፣ ስታዲየሞችና መሰል ሥፍራዎች ላይ ገደቦች አይኖሩም።
  • የሆስፒታል ጉብኝቶች የሚፈቀዱት ሙሉ ክትባቶችን ለተከተቡ ብቻ ይሆናል፤ ላልተከቡ ሰዎች ልዩ የሆስፒታል ጉብኝት ፈቃድ የሚሰጠው ሊጎበኙት የሚሹት ሰው የሕይወት ፍፃሜ ላይ ወይም ድንገተኝ አደጋ ላይ ያለ ከሆነ ብቻ ይሆናል።
  • ሙሉ ክትባት የተከተቡ የኩዊንስላንድ ነዋሪዎች የፊት ጭምብል ለማጥለቅ ግድ የሚሰኙት በበረራ ወቅትና አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ ይሆናል። 
  • ባለ ሶስት ደረጃ ፍኖተ ካርታን ተመርኩዞ ኖርዘን ቴሪቶሪ ውስጥ ከኖቬምበር 23 ጀምሮ የቤት ውስጥ ወሸባ ይጀመራል።

የኮቪድ-19 ተጠቂዎች፤

  • ቪክቶሪያ ውስጥ 1,069 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ 10 ሕይወታቸውን አጥተዋል።
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ 222 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውንና አራት ለሞት መዳረጋቸውን አስመዘገበች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 

 

 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service