- ቪክቶሪያ የመጀመሪያ ዙር 80 ፐርሰንት የክትባት ዒላማዋን አለፈች
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ይዛ ከነበረው ዕቅድ አንድ ሳምንት ቀደም ብላ ትምህርት ቤቶችን ልትከፍት ነው
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከዕኩለ ለሊት በኋላ ሊረግብ ነው
- ኩዊንስላንድ ስድስት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,438 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁት የአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ የመጨረሻ ውድድር በተካሄደበት የሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቡድን ከመሰባሰብ ጋር የተያያዘ ነው። የአምስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።
ክስተቱን አስመልክቶ የቪክቶሪያ ኮቪድ-19 ኮማንደር ጄሮን ዌይማር ለቪክቶሪያ ከገደብ መውጪያ ዕቅድ "ብርቱ" የኋሊዮሽ ምልሰት እንደሆነ አበክረው ገልጠዋል።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ቪክቶሪያ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በቂ የፋይዘር ክትባት አቅርቦት ስለሚኖራት በመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባቶች መካከል የነበረውን የስድስት ሳምታት ክፍተት ወደ ሶስት ሳምንታት ዝቅ እንደሚል አስታውቀዋል።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 941 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የሙዋዕለ ሕፃናት፣ አንደኛ ክፍልና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተያዘላቸው የትምህርት ቤት መመለሻ ጊዜ ቀደም ብለው ከኦክቶበር 18 ጀምሮ ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።
የተቀሩት ሌሎች ተማሪዎች ከሁለት ሳምንታት በኋላ ኦክቶበር 25 እና ኖቬምበር 1 ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ይመለሳሉ።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 31 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች።
ከዓርብ ኦክቶበር 12:01am ጀምሮ ከቤት ውጪ የመዝናኛ ሰዓታት ይራዘማሉ፣ ብሔራዊ ፓርኮች ይከፈታሉ፣ ለችርቻሮ ንግዶች ተጨማሪ ድጎማች ይደረጋሉ፣ ሌሎች ገደቦችም ይረግባሉ some restrictions will ease
ዕድሜያቸው ከ60 በላይ ያሉ ነዋሪዎች የፋይዘር ክትባት መከተብ ይችላሉ።
የኮቪድ-19 ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ to book your COVID-19 vaccination.
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የ Brisbane, Gold Coast, Logan, Moreton Bay, Townsville እና Palm Island አካባቢ መንግሥታት ከዛሬ ሐሙስ 4pm ሴፕቴምበር 30 ጀምሮ የደረጃ 2 ገደቦች ተጥሎባቸዋል enter stage 2 restrictions
- የፌዴራል መንግሥቱ ሥራቸውን ላጡ ሠራተኞችና ንግዶች ይሰጥ የነበረው የኮቪድ-19 አደጋ ድጎማ ሁለተኛ ዙር ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ሲደርስ እንደሚያበቃ አስታወቀ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

