የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ሶስት ዙር ክትባት በሙሉ ክትባትነት የመፈረጁ ጉዳይ 'ከአለመሆኑ ይልቅ መሆኑ' እንደሚያመዝን ተጠቆመ

*** የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልበኒዚ የአረጋውያን ክብካቤ ግልጋሎቶች ሚኒስትር ሪችድ ኮልቤክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅትን በብቃት አልተወጡም በማለት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠየቁ።

COVID-19 update

A woman is seen receiving a vaccination at a Cohealth pop-up vaccination clinic at the State Library Victoria, in Melbourne. Source: AAP

  • አውስትራሊያ ውስጥ የሶተኛ ዙር ኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዕድሜያቸው 16 እና 17 ያሉ ልጆች ቁጥር 8.4 ሚሊየን አለፈ።
  • የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ሙሉ ክትባት ሶስተኛ ዙር ክትባትን ያካተተ እንዲሆን በአውስትራሊያ የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር ይሁንታን የማግኘቱ ጉዳይ "ከአለመሆኑ ይልቅ መሆኑ" እንደሚያመዝን ተናገሩ። 
  • የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልበኒዚ የአረጋውያን ክብካቤ ግልጋሎቶች ሚኒስትር ሪችድ ኮልቤክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅትን በብቃት አልተወጡም በማለት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠየቁ።
  • የአውስትራሊያ ዋና የጤና ኃላፊ ሰዎች የኦሚክሮን ማዕበልን የኮሮናቫይረስ መጨረሻ አድርገው እንዳይመለከቱ አሳሰቡ።
  • አክለውም፤ አዲስ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና ከ2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጉንፋን ወረርሽኝ እንደሚከሰት አመላክተዋል። 
  • ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ ትምህርት ቤቶች በተከፈቱ ጥቂት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችና በደርዘኖች የሚቆጠሩ መምህራን ለሁለት ሳምንታት ወሸባ ለመግባት ግድ ተሰኙ። ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ 19 ስዎች በቫይረስ መያዛቸው ተመዝግቧል። 
  • ኒውዝላንድ በአምስት ደረጃ ዕቅድ ድንበሮቿን ከፌብሪዋሪ 27 ጀምሮ ትከፍታለች፤ በወርኃ ኦክቶበርም ሙሉ በሙሉ ድንበሮቿ ለዓለም አቀፍ መንገደኞች ክፍት ይሆናሉ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 12,632 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ360 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,578 ሕመማን 1 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 12,157 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 34 ሕይወታቸውን አጥተዋል።  ሆስፒታል ከሚገኙት 752 ሕመማን 82 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ኩዊንስላንድ 8,643 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 9 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 749 ሕመማን 47 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ደቡብ አውስትራሊያ 1,583 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ 226 ሆስፒታል ይገኛሉ።

ታዝማኒያ፣ ደቡብ አውስትራሊያና ኖርዘን ቴሪቶሪ እያንዳንዳቸው አንድ የሟች ቁጥር አስመዝግበዋል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

NSW 
ACT 
 

 






Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service