- ቪክቶሪያውያን ዛሬ የሚነሱ ገደቦችን እየጠበቁ ነው
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ነዋሪዎች ሃለዊንን የኮቪድ-ጥንቃቄ በተመለበት መንገድ እንዲያከብሩ አሳሰቡ
- ቪክቶሪያ የኮቪድ-19 ክትባት ያለመከተብን አስባቦችን እያጠበቀች ነው
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,656 ነዋሪዎች በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ቪክቶሪያ ዛሬ ከምሽቱ 6 pm ጀምሮ ተጨማሪ ገደቦችን ታነሳለች።
በጣም አስፈላጊ ያልሆኑ ችርቻሮዎች ከሳምንታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይከፈታሉ፤ ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶችና ካፌዎች የመስተንግዶ አቅማቸው ይጨምራል።
በሜልበርና ሪጂናል ቪክቶሪያ መካከል ተጥሎ የነበረ የጉዞ ገደብ ያከትማል። በመላ ቪክቶሪይ የመዘዋወር እገዳ አይኖርም። የሪጂናል ቪክቶሪያ ነዋሪዎች ለሜልበርን ዋንጫ ወደ ሜልበርን ከተማ መምጣት ይችላሉ።
የፊት ጭምብል የማጥለቅ ግዴታ አይኖርም፤ ሆኖም ርቀትን መጠበቅ በማይቻልባቸው የቤት ውስጥ ኩነቶች የፊት ጭምብል የማጥለቅ ግዴታ ይኖራል።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 268 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሃለዊን የኮቪድ-ጥንቃቄ በተመለበት ሁኔታ ማክበር ይቻላል። ለልጆች የሚሰጡ ከረሜላዎች የታሸጉ መሆን ይገባቸዋል።
የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ አሁኑኑ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 10 ነዋሪዎች በቫይረስ መጠቃታቸውን መዝግባለች፤ በጠቅላላው 234 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።
- የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ባሕር ማዶ የተወለዱ ሰዎች የኮቪድ-19 የሞት መጠን ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 4.2 ሲሆን፤ አውስትራሊያ የተወለዱ 2.0 መሆኑን ገለጠ።
- ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት ላለመከተብ ሐኪሞች ዘንድ እየሄዱ የሕክምና ማስረጃ እንዲሰጣቸው የመጠየቅ አስባቦች መበርከትን ተከትሎ የቪክቶሪያ መንግሥት ደንቦችን እያጠበቀ ነው።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

