የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ ከፍተኛ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር አስመዘገበች

*** በዚህ ሳምንት መጨረሻ እሑድ ዕለት ብሪስበን የሚካሔደውን የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የመጨረሻ ውድድር ለመመልከት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ከጤና መመሪያዎች ውጪ በየግል መኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንዳይሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

COVID-19 update

People are seen crossing Bourke Street in Melbourne. Source: AAP

  • ክቶሪያ ውስጥ 1,488 ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 813 በቫይረስ ተያዙ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 52 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል
  • ኩዊንስላንድ ወሸባ ያሉ ሁለት ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸውን አስመዘገበች

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,488 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የሁለት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከፍተኛው ዕለታዊ አኃዝ ሆኖ ተመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት 429 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ሲሆን 97ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል 54ቱ በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።    

በርካታ የሕክምና ተቋማት ዋራንቡል፣ ሼፐርተን፣ ጊስቦርን፣ ኢስት ቤንዲጎ፣ ሙካታህ እና ባላራትን ጨምሮ የቪክቶሪያ ከፍተኛ ኮቪድ ተጋላጭነት ሥፍራዎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው Victoria's COVID exposure site list 

በጅሮንድ ቲም ፓላስ የግለሰብ ንግዶችን ጨምሮ መመዘኛ ለሚያሟሉ ንግዶች የአንድ ጊዜ ክፍያ ድጎማ የሚውል $196.6 ሚሊየን መመደቡን አስታወቁ። ድጎማው ያስፈለገው ከሴፕቴምበር 21 እስከ ኦክቶበር 4 ከተጣሉ ገደቦች ጋር ተያይዞ ነው።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 831 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 1,005 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን 202ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል 99ኙ በመተፈንሻ መሳሪያ እየተረዱ ናቸው።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ተወካይ ዶ/ር ጀርሚ ማክአኑልቲ በዚህ ሳምንት መጨረሻ እሑድ ዕለት ብሪስበን የሚካሔደውን የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የመጨረሻ ውድድር ለመመልከት ነዋሪዎች ከጤና መመሪያዎች ውጪ በየግል መኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንዳይሰባሰቡ አሳስበዋል። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 52 ሰዎች በኮቪድ-19 ተጠቅተዋል፤ 29ኙ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
  • የኩዊንስላንድ ባለስልጣናት ወሸባ ውስጥ የነበሩ ሁለት ልጆች በብሪስበን አቬይሽን ከተከሰተው ቫይረስ ጋር በተያያዘ መጠቃታቸውን አስታወቁ። 
  • የኩዊንስላንድ ጤና ሚኒስትር ኢቬት ዳት ነገ የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የመጨረሻ ግጥሚያ በሚካሔድበት ስታዲየም ዙሪያ ተንቀሳቃሽ የክትባት ክሊኒኮች እንደሚቆሙ ገለጡ።

COVID-19 update
Source: SBS
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 


Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ ከፍተኛ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር አስመዘገበች | SBS Amharic