የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - አውስትራሊያ ለዓለም አቀፍ ተማሪዎችና የሥራና ሽርሽር ባለቪዛዎች የቪዛ ክፍያ ተመላሽ ልታደርግ ነው

*** የሜልበርን አውሮፕላን ማረፊያ ሁለት ዙር ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች የቅድመ በረራ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲቀር ጥሪ አቀረበ

COVID-19 update

People wearing PPE arriving at Sydney International Airport in Sydney. Source: AAP

  • ከዛሬ ጀምሮ ወደ አውስትራሊያ የሚመጡ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችና የሥራና ሽርሽር ባለቪዛዎች ለቪዛ የፈጸሙት ክፍያ ተመላሽ ይሆንላቸዋል፤ ይህ የሚሆነውም ሌሎችም ወደ አውስትራሊያ ፈጥነው እንዲመጡ ለማበረታት ነው
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የተደረጉት ለውጦች በኦሚክሮን መዛመት ሳቢያ አገሪቱን ገጥመዋት ያሉትን የሠራተኛ ኃይል እጥረቶች ለመግታት እንደሆነ አስታውቀዋል
  • ክፍያዎቹ ነፃ ሆነው የሚቆዩት ከረቡዕ ጀምሮ በስምንት ሳምንታት ውስጥ ለሚዘልቁ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች፤ እንዲሁም ለሥራና ሽርሽር ባለቪዛዎች እስከ 12 ሳምንታት ባሉት ጊዜያት ይሆናል
  • ሶስት በርካታ ነዋሪዎች በሚኖሩባቸው የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት ውስጥ 61 ሰዎች በኮቪድ-19 ተጠቅተው ሕይወታቸውን አጥተዋል 
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 32 ሰዎች ለሞት ሲዳረጉ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,863 ሕሙማን ውስጥ 217 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛሉ
  • ፕሪሚየር ዶሚኒክ ፐሮቴይ ከዛሬ ጀምሮ ሁለተኛ ክትባታቸውን ከተከተቡ ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ወራት የሞላቸው የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች የሶስተኛ ዙር ክትባታቸውን መከተብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል
  • የአውስራሊያ ዋና የሕክምና መኮንን ፕሮፌሰር ፖል ኬሊ መጪው ክረምት እንደ ጉንፋን ከመሳሰሉ ዓመታዊ ተላላፊ በሽታዎች ጋር ተዳምሮ የኮሮናቫይረስ እንዲያገረሽና አዲስ ቫይረስም እንዲከሰት ሊያደርግ እንደሚችል አመላከቱ 
  • ኩዊንስላንድ ከቅዳሜ 1am ጀምሮ ሁለት ዙር ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች ወሸባ መግባት እንዲቀርላቸው ልታደርግ ነው
  • ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼይ ቀኑ የተመረጠው የከፍለ አገሪቱ ሁለት ዙር ተከታቢዎች ቁጥር በመጪዎቹ ቀናት 90 ፐርሰንት ስለሚደርስ መሆኑን ገልጠዋል
  • የሜልበርን አውሮፕላን ማረፊያ ሁለት ዙር ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች የቅድመ በረራ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲቀር ጥሪ አቀረበ፤ እስካሁን በአለው አሠራር መንገደኞች ከጉዟቸው ሶስት ቀናት ቀደም ብሎ ከቫይረስ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ የPCR ምርመራ ውጤታቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤ 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 32,297 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ32 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 20,769 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 19,932 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 11 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።

ታዝማኒያ 1,185 ሰዎች ተጠቅቶባታል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

NSW 
ACT 

Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service