የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ምዕራብ አውስትራሊያ ወሰኔን አልከፍትም አለች፤ የ80 አውስትራሊያውያን ሕይወት በአንድ ቀን በኮሮናቫይረስ አለፈ

*** 30 ያህል የአፍሪካ፣ እስያና መካከለኛ ምሥራቅ መደበኛ መድኃኒት አምራቾች ርካሽ የኮቪድ-19 ኪኒን ሊያመርቱ ነው።

COVID-19 update

WA Premier Mark McGowan speaks during an announcement in Perth, Monday, December 13, 2021. Source: AAP

  • የምዕራብ አውስትራሊያ ፕሪሚየር ማርክ ማክጎዋን መላ አውስትራሊያ ውስጥ ኦሚክሮን ንሮ ባለበት ወቅት ፌብሪዋሪ 5 የክፍለ አገራቸውን ወሰን ለመከፈት በሰጡት ቃል መርጋት ማለት "ደንታ ቢስነትና የኃላፊነት መጉደል" እንደሚሆን ተናገሩ። 
  • አቶ ማክጎዋን በሁለት ዙር ክትባቶች ብቻ ኦሚክሮንን የመቋቋም ውስንነት ያሳሰባቸው መሆኑን አመላክተው፤ የሶስተኛ ዙር ክትባት መጠን ከፍ እስከሚል ድረስ ጊዜ እንደሚያሻ ገልጠዋል። 
  • ሆኖም የአውስትራሊያ ሕክምና ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ኦማር ኮሺድ የአቶ ማክጎዋን ውሳኔን በመቃወም የክፍለ አገሪቱ ወሰን "ክፍት ሊሆን ይገባል" ብለዋል።  
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ 46 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ዛሬ ዓርብ አስታወቀች። ይህም ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ የተመዘገበ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር መሆኑ ተጠቅሷል። እንዲሁም፤ ቪክቶሪያ 20፣ ኩዊንስላንድ 13 ታዝማኒያ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አስታውቀዋል። 
  • ባለፉት 24 ሰዓታት ኒው ሳውዝ ዌይልስ እና ቪክቶሪያ ውስጥ የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥር ቀንሷል። የቪክቶሪያ ሆስፒታል ሕሙማን ከ 1,206 ወደ 1,096 በዘጠኝ ፐርሰንት ዝቅ ሲል፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሕሙማን ቁጥር ከ 2,781 ወደ 2,743 በመውረድ ከአንድ ፐርሰንት በላይ ቀንሷል። 
  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና የጤና መኮንን ኬሪ ቻንት የቫይረሱ ማኅበረሰቡ ውስጥ የመስፋፋት ፍጥነት እያዘገመ መሆኑን "የተለያዩ አመላካቾች" መኖራቸውን ጠቆሙ። 
  • የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼይ ከሰኞ ጀምሮ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ ክትባታቸውን ከተከተቡ ሶስት ወራት ያስቆጠሩ ነዋሪዎች ለሶስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት መመዘኛን እንደሚያሟሉ ገለጡ። 
  • የአውስትራሊያ ፌዴራል ፖሊስ በፈጣን አንቲጄን መመርመሪያ ላይ የናረ ዋጋ ተጨምሮ የሚካሔደውን ሽያጭ አስመልክቶ ምርመራ ጀመረ።
  • የቪክቶሪያ ፓራሜዲክ እና የስልክ ጥሪ ማዕከል ኦፕሬተር ሠራተኛ ማኅበር የአምቡላንስ ስልክ ጥሪ ተቀባዮች ቁጥር አነስተኛነት መሆኑን አሳሰበ። 
  • 30 ያህል የአፍሪካ፣ እስያና መካከለኛ ምሥራቅ መደበኛ መድኃኒት አምራቾች የመርክ እና ኩባንያው ኮቪድ-19 ርካሽ ኪኒን ሊያመርቱ ነው። ይህም የሚሆነው በተባበሩት መንግሥታት ደሃ አገራት ወረርሹኙን ለመከላከል ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖራቸው በተደረሰው ስምምነት መሠረት ነው።  
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤ 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 30,825 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ25 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 20,769 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 16,812 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ ዘጠኝ ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።

ታዝማኒያ  927 ሰዎች ተጠቅቶባታል።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 892 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውን አስመዝግባለች

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

NSW 
ACT 

Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service