- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከእንደራሴዋ የማሳሰቢያ ቃል ጋር ገደቦቿን አረገበች
- ቪክቶሪያ አዲስ የክትባት ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጀመረች
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ከወሸባ ወጡ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 496 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ክፍለ አገሪቷ ለ100 ቀናት በገደቦች ስር ከቆየች በኋላ የአካል ማጠንከሪያ ማካሄጃዎች፣ ካፌዎች፣ ምግብ ቤቶች፣ ሱቆችና የፀጉር መስተካከያዎች ዳግም ሊከፈቱ ችለዋል።
እንደራሴ ዶሜኒክ ፔሮቴይ ንግዶች በተቻለ መጠን ከደንበኞች የሚቀርቡላቸው የክትባት መረጃዎች ትክከለኛ መሆናቸውን ማረጋጋጥ እንዳለባቸው አክለዋል።
ገደቦቹ የከፍለ አገሪቱን ምጣኔ ሃብት በሳምንት $1 ቢሊየን ያሳጣ ሲሆን እንደራሴው እንዲያም ሆኖ የሠራተኛች እጥረት መኖሩን አመላክተዋል።
የዓለም አቀፍ ድንበሮችን በመክፈቱ ረገድም ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
"ከሌላው ዓለም ተነጥለን መኖር አንችልም፤ አውስትራሊያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንሻለን" ብለዋል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
Find a vaccination centre near you.
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,612 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የስምንት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተከታተሉ ካሉ 667 ሕሙማን ውስጥ 133ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ያሉ ሲሆን 94ቱ የመተንፈሻ መሳሪያ ተገጥሞላቸው ይገኛሉ።
እሑድ ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ 81,000 ሰዎች ክትባት ተከትበዋል።
ባለ ስልጣናት ወጣቶች ቤተሰቦቻቸውን ክትባት እንዲከተቡ በማሳመኑ ረገድ ጥረት እንዲያደርጉ እያሳሰቡ ነው።
የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ የሞደርናና ፋይዘር ቪክቶሪያ ውስጥ ላሉ ለሁሉም የዕድሜ ገደብ የሚሰጥ መሆኑን ገለጡ። ቪክቶሪያ 'ክትባት ቲኬት ነው' በሚል አንድ አዲስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጀምራለች።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 32 ሰዎች በቫይረስ ተጠተዋል። ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ነዋሪዎች 97.8 ፐርሰንት ክትባት ተከትበዋል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ግለሰብ በቫይረስ አልተያዘም።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

