"ሕግ የማስከበር ሥራን የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ ማቅረብ ስህተት ነው" - ሚኒስትር ቀነአ ያደታ

*** የአገር መከላከያ ሚኒስትር ቀንአ ያደታ መግለጫ

DM Kenea Yadeta

Kenea Yadeta, Minister for Defence Source: PD

የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሚኒስትር ቀንአ ያደታ መግለጫ እየሰጡ ነው።

ሚኒስትሩ ጦርነቱ ተራ ወንጀለኛን የማፈላለግ ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የጣለን ፅንፈኛ ቡድን አድኖ የመያዝ ግብ ያለው" ነው ብለዋል።

"ፅየሃሰት መረጃዎቹን ማሰራጨት የጀመረው ቡድን የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ÷ "ከውጭ ሀገር ጋር ሆኖ የትግራይን ህዝብ እየወጋ ነው የሚል የማይጨበጥ ወሬ ያሳራጫል" ሲሉ ገልጠዋል።

"ሰራዊቱ በታላቅ ጥንቃቄና ሙያዊነት ቡድኑን ነጥሎ ለማጥቃት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ሰአት ንፁሃንን እና መሰረት ልማት ላይ ጥቃት ይፈፅማል የሚል ማደናገሪያንም እየነዛ" መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሄው ቡድን ህግ የማስከበር ስራውን የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ ማቅረቡን ያነሱት ሚኒስትሩ ይህም ስህተት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም "የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ የማንንም የውጭ ኃይል ድጋፍ ሳይፈልግ የጥፋት ቡድኑን የመደምሰስ ቁመና እንዳለው"ም ጠቁመዋል፡፡

 "በዚህም ሰራዊቱ የትኛውንም ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ ድጋፍ አያስፈልገውም ቡድኑን ለማጥቃት የውጭ ድጋፍ አልጠየቀም አይጠይቅምም" ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ መከላከያ ሰራዊቱ የሚወስደውን ህግን የማስከበር እርምጃ በጥንቃቄ እያከናወነ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

የትግራይ ህዝብ የጥፋት ቡድኑን ሴራ በመገንዘብ ለጉዳት እንዳይዳረግም አሳስበዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት በዘራፊው የህወሓት ቡድን ላይ በርካታ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል ያሉት ቀንአ ያደታ ህዝቡ እያሳየ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የትግራይ ልዩ ሀይልም አጥፊ ቡድኑን አሳልፎ በመስጠት ህዝብና ሀገርን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

 


Share

Published

Updated

By Stringer

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
"ሕግ የማስከበር ሥራን የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ ማቅረብ ስህተት ነው" - ሚኒስትር ቀነአ ያደታ | SBS Amharic