የሰላም ፣ የአንድነት፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ መገለጫ መሆኑ የተገለፀው ኢፍጣር መርሐግብር በመስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ በመርኃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት "ይህ የዛሬ ኢፍጣር በሃገራችን ከዚህ ቀደም ያልታየ ስለሆነ በጣም ደስ የሚል ዝግጅት ነው። ለአንድነት፣ ለሰላም እና ለፍቅር እንድትቆሙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን አደራ እላለሁ" ብለዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ " ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የሁላችንም ሃብቶች ናቸው ተአቶ ሁላችንም ልንጠብቃቸው ይገባል። ፕሮግራሙ ባለመናበብ ምክንያት ሳይካሄድ ቢቀርም ዛሬ ባማረ መልኩ ለመካሄድ በቅቷል ነው። በመዲናችን በቀላሉ እሳት መጫር ይቻላል ብለው ለሚያስቡ አካላት እንደማይሳካ የሃይማኖት አባቶች አሳይተዋል" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Source: SM