የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደ አውሮፓዊያን የዘመን ቀመር በ2015 ላይ በፓሪስ የተደረሰውን ስምምነት እንደ አሜሪካ እና አውሮፓ ያሉ ግዙፍ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች በገቡት ቃል መሰረት ስምምነቱን እየተገበሩት ስላልሆነ የዓለም ሙቀት መጨመር አሳስቦኛል እያለ ሲወተውት ቆይቷል። የዓለምን ሙቀት መጨመረ የሚከታተሉት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ምንም እንኳ የፓሪሱ ስምምነት የዓለምን ሙቀት ከ2 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ እንዳይጨምር ለማደረግ ቃል የተገባ ቢሆንም፤ መሆን የነበረበት ግን ከ1.5 ዲግሪ ሴሊሺየስ በታች ነበር። ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው፡፡
በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠባቸው 95 በመቶ የሚሆኑት ከተሞች በአፍሪካ እና በእስያ የሚገኙ ናቸው። የ20 ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያዋ የናይጄሪያዋ ሌጎስ እና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መዲና ኪንሻሳ የመሳሰሉት በፍጥነት እያደጉ የሚገኙ ከተሞች ይገኙበታል።
ተመራማሪዎች በተደጋጋሚ እንደሚያስገነዝቡት የአየር ብክለትን ለመቀነስ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ መኪኖችን ማሽከርከር፤ አጭር ርቀቶችን ደግሞ በእግር መጓዝ አሊያም ብስክሌት መጠቀምና አነስተኛ የካርበን ልቀት ያላቸውን የቤት ውስጥ መገልገያዎችን መምረጥ ተገቢ ነው፡፡
ከሰሞኑ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን መፈብረክ ለአየር ንብረት ለዉጥ ፖሊሲ የሚኖረውን ፋይዳ በተመለከተ በአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕረስ ማዕከል /FOREIGN PRESS CENTER/ አማካኝነት ከመላው ዓለም ለተውጣጡና በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ አተኩረው እየዘገቡ ለሚገኙ 50 ጋዜጠኞች አሜሪካ በተለያዩ ፈጠራዎች በመታገዝ እየሰራች ያለችውን ጥረት በተመለከተ ልዩ የበይነ መድረክ ጉብኝት ( virtual tour ) ገለፃ ተደርጎ ነበር።
በውይይቱ በአሜሪካ የኢኖቬሽን ዘርፍ ልምድ የተገለፀ ሲሆን ግዙፉ ኩባንያ ጄኔራል ሞተርስ እንደማሳያ ለጋዜጠኞች ልምዱን እንዲያጋራ ተደርጓል።
ለረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በዘርፉ እየተከናወኑ ስላሉ ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ቶም ኮኒ በጄኔራል ሞተርስ የዓለም የሕዝብ ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ሚስተር ኮኒ ጀነራል ሞተርስ በዓለም ዙሪያ ኢንቨስት በሚያደርግበት እና በሚያንቀሳቅስባቸው ሀገሮች ሁሉ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ የፖሊሲ እና የቁጥጥር መፍትሄዎችን ለማሳካት ከውጭ መንግስታት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮኒ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር ለ 25 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ሥራ ከሠሩ በኋላ ጄኔራል ሞተሮችን ተቀላቅለዋል ፡፡
እርሳቸው እንደጠቀሱት ከአራት ዓመት በፊት ማለትም በ 2017 “ዜሮ ፣ ዜሮ ፣ ዜሮ” የምንልበትን ራእይ መዘርጋታውን ያስታውሳሉ፡፡ ዜሮ ብልሽቶች ፣ ዜሮ ልቀቶች እና ዜሮ መጨናነቅ።

In this photo illustration, a General Motors Company logo seen displayed on a smartphone and in the background. Source: Getty
ሚስተር ኮኒ እንደሚሉት እንደ አውሮፓዊያን የዘመን ቀመር በ 2040 ከካርቦን ገለልተኛ የመሆን እቅድ አላቸው፡፡ ያ ማለት መርከቦቻቸውን እንዲሁም ኦፕሬሽኖቻቸውን እና ተቋሞቻቸውን ማለት ነው ፡፡ ሁሉም ኤሌክትሪክ፣ ዜሮ ልቀቶች ለማድረግ በሂደት ላይ ነን ብለዋል፡፡ እኛ እ.ኤ.አ. በ 2025 30 ሁሉንም ኤሌክትሪክ ሞዴሎችን ለማስተዋወቅ ግዴታችንን ተወጥተናል ወይም ቃል ገብተናል ፡፡ ያ ከአራት ዓመት በኋላ ብቻ ነው ሲሉም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ፡፡
ኢንዱስትሪ በሚቀየርበት ጊዜ ሁሉ የመንግስት ማበረታቻዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውንም በውይይቱ ተነስቷል፡፡ ኖርዌይን ለአብነት በመጥቀስ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ ኖርዌይ የ 54 በመቶ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤትነት መጠን አላት ፣ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡
አሁን የኖርዌይ ቀመር ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ላይመሳሰል ይችላል፡፡ እሱ የግድ ከአሜሪካ ጋር የሚስማማ አይደለም ፣ ግን ለማጥናት እና ከዚያ ለመማር ብዙ እድል እንዳለም በውይይቱ ተንሸራሽሯል ፡ ከኖርዌይ ተሞክሮ እና ከሌሎች ሀገሮች የተገኙ ቁልፍ ልምዶችና መንገዶች የሸማቾች ማበረታቻዎች እጅግ አስፈላጊ ስለመሆናቸውም እንዲሁ፡፡
በአሜሪካ ውስጥ ከፌዴራል መንግሥት የመጡ አዲስ የኢቪ (የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች) ገዢዎች የ 7,500 ዶላር የሸማች ማበረታቻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም 50 ግዛቶች አሉ ፣ እና አንዳንድ ግዛቶች የ “ኢ.ቪ” ማበረታቻዎች ወይም የግብር ምዝገባዎች ወይም ለ ‹ኢ.ቪ› ግዢ ቅናሽ አላቸው ፣ ይህ ሁሉ በአሜሪካ የባይደን ሃሪስ አስተዳደር የአየር ንብረት ለውጥን ለማገዝ የታቀደ ስለመሆኑም ከተለያዩ ዓለም ሃገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች በተሳተፉበት የበይነ መረብ መድረክ ላይ ተብራርቷል፡፡
የዓለማችን የወቅቱ ፈተና የሆነው የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ብክለት በሃያላን ሃገራት ዘንድ በተሰጠው ትኩረት ልክ ወደተግባር ተገብቶ ከተጋረጠብን ችግር እንወጣ ይሆን? በዘርፉ ትኩረት ያደረጉ ጋዜጠኞችስ በሚሰሩባቸው ተቋማት ተጽእኖ ፈጣሪ ዘገባዎችን እያጠናቀሩ መፍትሄ እንዲመጣ ሚናቸውን ያጎሉ ይሆን? በጊዜ ሂደት የምናየው ጉዳይ ይሆናል፡፡
[ ደመቀ ከበደ ፡ የበይነ መረብ ውይይቱ ተሳታፊ ]