የጎንደር ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ፤ ጎንደር የቱሪዝም መዳረሻዋን ከተማ የበለጠ ውበትና ድምቀት የሆነውን ጥምቀት ወደፊትም ከዚህ በበለጠ ውብና ደማቅ የቱሪስቱም መደሰቻ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥምቀትን ስናከብር የኢትዮጵያ አንድነትን በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

Source: Demeke Kebede
አቶ አገኘሁ እንዳሉት በአምናው ጥምቀት አከባበር ባጋጠመው የደረጃ መደርመስ ለህልፈት የተዳረጉትን ፣ በዚህ ዓመቱ የህግ ማስከበር ዘመቻ ህይወታቸው ያለፉትን፣ እንዲሁም በማንነታቸው ምክንያት ለመፈናቀልና ለሞት የተዳረጉትን ወገኖቻችንን ልናስባቸው ይገባል።
የአርባ አራቱ አድባራት ታቦታት በጎንደር ቅዱስ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር አድረው ዛሬ በድምቀት በምዕመኑ ታጅበው ወደየ አጥቢያ ቤተክርስትያናቱ ተሸኝተዋል።