SKIP TO MAIN CONTENT

ሙሉ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ልዩ ፈቃድ ሳይጠይቁ ወደ ውጭ አገር መሔድና መመለስ እንዲችሉ ተፈቀደ

*** ሲንጋፖር ከኖቬምበር 8 ጀምሮ ሙሉ የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ወሸባ የመግባት ግዴታ ሳይኖርባቸው ሲንጋፖርን መጎብኘት እንዲችሉ መፍቀዷን አስታወቀች።

COVID-19 update
Source: Qantas

1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

ሙሉ የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ለልዩ ይለፍ ፈቃድ ሳያመልክቱ ወደ ውጭ አገር መሔድና መመለስ እንዲችሉ ተፈቀደ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ከኖቬምቨር 1 ጀምሮ የልዩ ፈቃድ ጥየቃ እንደሚያበቃ አረጋግጠዋል።

ይህንኑ አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አውስትራሊያ በፈንታዋ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሲናፖራውያን ወደ አውስትራሊያ እንዲመጡ ለመፍቀድ መቃረቧንና ከአንድ ሚሊየን ተኩል በላይ አውስትራሊያውያን ዓለም አቀፍ የክትባት ምስክር ወረቀትን ተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ላይ የጫኑ መሆኑን ተናግረዋል። 

የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንትም በበኩላቸው፤ አውስትራሊያውያን ወደ ባሕር ማዶ ሲጓዙ ዕውቅና ያለው ሁለት ዙር ክትባት መከተባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሊይዙ እንደሚገባና የሁለተኛ ዙር ክትባታቸውን ሊከተቡ የሚገባውም ቢያንስ ወደ ውጭ አገር ለመሔድ ከመነሳታቸው አንድ ሳምንት በፊት መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። 

 

 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now