በአውስትራሊያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ሴቭ ኢትዮጵያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲሆን በመላው አስስትራሊያ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰበውን ከ153ሺ ዶላር በላይ ወይም ከ7.6 ሚሊዮን ብር በላይ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስረከበ።
ድጋፉን በሚያስረክቡበት ወቅት የማህበሩ አባላት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ድጋፍ ከአንድ መድረክ የተሰባሰበ ሀብት መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቋሚነት ከገቢያቸው ሀገራቸውን መደገፍ የሚችሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስም በበኩላቸው በአውስትራሊያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው በመምጣታቸው እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ሃብት በማሰባሰባቸው ምስጋናቸውን ገልጸዋል። አክለውም ዳያስፖራዎቹ በየወሩ በመደበኛነት በሚደረግ መዋጮ በቋሚነት ሀገራቸውን ለመደገፍ የጀመሩት እንቅስቃሴ በሌሎች አካባቢዎችም ሊስፋፋ የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዲያስፖራ ኤጀንሲ