"የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር ተደናግጠናል" በጀርመን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት

*** የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና የአውሮፓ ሕብረት ገንቢ ለሆነው ትብብርና ለብሔራዊ ሉዓላዊነት ክብር ያደረጋችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን

Letter tp President Trump

Prof Dr Asnakech Seyoum (L) and Dr Tsegaye Degneh (R) Source: AS and TD

ክቡራትና ክቡራን

እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር 2020 ዓ.ም ለቻንስለር ዶ/ር አንገላ መርከል በጻፍነው ግልጽ ደብዳቤ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌት ዙሪያ የወጣ የተዛባ ሪፖርት ላይ ያለንን ስጋት ገልጸናል። ደብዳቤው በጀርመን በሚኖሩ 60 ኢትዮጵያውያን እና ጀርመን-ኢትዮጵያውያን፣ የተቋማት፣ የኮሚኒቲዎችና የማህበራት ተወካዮች፣ የተለያዩ ትምህርቶች አካዳሚሻን፣ አርቲስቶች እና ኢንተርፕሩነሮች የተፈረመ ነው።

ይህ ከሆነ የተወሰነ ጊዜ ያለፈ ሲሆን፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌትም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። እስካሁንም በሱዳንና በግብጽ ሊከሰት ይችላል የተባለው ስጋት ሳይፈጠር ቀርቷል። በተቃራኒ ሱዳን እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 2020 ዓ.ም የክፍለ ዘመኑን ጎርፍ አይታለች። እንደ ተ.መ.ድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ የዓባይ ወንዝ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በ17.5 ሜትር ከፍተኛውን የውሃ ከፍታ ደርሷል። በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መያዝ በተቻለው የ4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ምክንያት ሊደርስ የሚችለው ጥፋት ቀንሷል።

የአየር ንብረት አጥኝዎች በዓለም ሙቀት ምክንያት በምስራቅ አፍሪካ የዝናብ መጠን እየጨመረ መሆኑን ታዝበዋል። በመሆኑም ግድቡ በቀጣይ በሱዳን ሊኖር የሚችልን ጎርፍ በመከላከልና ማስተካከል ረገድ ዋነኛ ሚና ይጫወታል።

የግድቡ ጠቀሜታ በተለይ በሱዳን ለሚገኙ ህብረተሰቦች ግልጽ የሆነ መሆኑና በኔቸር ገለልተኛ አጥኝዎች በቅርቡ በስፋት የተሰራጨ ጥናት (https://www.nature.com/articles/s41467-020-19089-x) ግድቡ ግብጽ ላይ ጉልህ ጉዳት ሳያደርስ ሱዳን እና ኢትዮጵያን እንደሚጠቅም አሳይቷል። በኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ የሚሰራው ሰራ መልካም ለውጥ እያሳየ ነው። በግድቡ ዙሪያ በግብጽ የሚታየው አመለካከትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዎንታዊ ለውጥ እየታየበት ነው።

ሆኖም ግን የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር ተደናግጠናል። እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 23 ቀን 2020 ዓ.ም ከእስራኤልና ሱዳን መንግስታት መሪዎች ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይትና በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች በስፋት በተሰራጨ ቪዲዮ ስለ ግድቡ የተናገሩ ሲሆን፣ በንግግሩም ግድቡ ወደ ግብጽ ውሃ እንዳይሄድ የሚያደርግ በመሆኑ ግብጽ ግድቡን ማፈንዳት አለባት ብለዋል።

ቃል በቃል፤ “It is a very dangerous situation because Egypt is not going to be able to live that way. They’ll end up blowing up that dam [...] I say it loud and clear, They’ll blow up that dam,” (የንግግሩን የዩትዩብ ማገናኛ (‘ሊንክ’) በዚህ ማግኘት ይችላሉ፤ https://youtu.be/XSxvCd7af-c). የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር እና ወቅታዊ ሁኔታ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ

ለኤሌትሪክ ማመንጫ የሚያገለግል ግድብ ሥራውን ለመፈጸም የግዴታ ውሀ መልቀቅ (ማሣለፍ) አለበት፣ ኘሬዘዳንት ትራምኘ ይህን የመሠለ ሀቅ አና ብዙ ሁኔታዎችን ያለተረዱ መሆናቸው ግልጽ ነው::

ግድቡ የቀጠናውን የውሃ አቅርቦት በሂደት የሚያሻሽል መሆኑ ላይ ኤክስፐርቶች ይስማማሉ። በ2020 ዓ.ም የነበረው ከባድ ዝናብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን የሙሊት ደረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድታሳካ አስችሏል።

ኢትዮጵያ ምክንያታዊ አጠቃቀምና ከፍተኛ ጉዳት በማያስከትሉ የፍትሃዊነት መርሆችን በማክበር የህዳሴ ግድብን የመሙላት እና የመጠቀም መብት አላት፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ለአባይ ውሃ 86% የምታበረክት ቢሆንም ከ65 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚዎች አይደሉም፡፡ ነገር ግን 98% ግብፃውያ የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ እንደግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለው የከርሰምድር ውሃ እንዲሁም የባህርን ውሃ ከጨው በመለየት ለመጠቀምም ባህር ስለሌላት አትችልም፡፡ የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሃይል የሚመነጨው ‘ከባዮማስ’ (ከአንጨት) በመሆኑ፣ ይኽም የደን መመንጠርን ፣ የአካባቢን (Environment) እና የመሬት መጎሳቆልን ፣ድርቅ ፣ ጎርፍና ረቂቅ የእንሰሳትና የሰው በሽታን ያስከትላል።

በአየር ንብረት ለውጥ እና በተዛባ ዝናብ ምክንያት ቁጥራቸው ወደ 8 ሚሊዮን ያህል ሰዎች በየአመቱ ለአስቸኳይ የምግብና ሰብአዊ ድጋፍ ጥገኞች ሆነዋል። ለኢትዩጵያ የግድቡ መገንባት እና የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ቅንጦት ሳይሆን ከሞት የሽረት ያህል አስፈላጊ ነው፡፡ በፍጥነት እያደገ ያለውን የህዝብ ብዛትና በአሁኑ ሰዓት ከ110 ሚሊዮን በላይ የሆነውን ህዝብ ከከፋ ድህነት ለማውጣት ግድቡ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባልፈረመችው ፣ በቅኝ ገዥዎች በተፈረመ ውል መሠረት ግብጽ የአባይን ውሀ ለመቆጣጠር የይገባኛል ደረቅ (ፍንክች የማይል) ጠንካራ አቋም ታሣያለች::

ግብጽ በግድቧ ውስጥ በጣም ብዙ ውሀ አላት፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የአስዋን ግድብ ውስጥ የተመዘገበ 40 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሚትር ያህል የውሀ ክምችት ይገኛል::

የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተያየትም በሁሉም ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ከፍተኛ ስጋት እና ቁጣ የቀሰቀሰ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና እኛ ፈራሚዎቹም እንደዚህ ዓይነት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚሰነዘሩ ዛቻዎች የተሳሳቱ፣ ፍሬያማ ያልሆኑ እና የዓለም አቀፍ ህግን የሚጥሱ ናቸው ብለን እናምናለን፡፡

የፕሬዚዳንቱ መግለጫ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ከመቶ ዓመት በላይ የሆነውን የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን አያንጸባርቅም ፡፡

ይህንን ደብዳቤ ለእርስዎ ስናቀርብ አሁን እየተከናወነ ያለውን ሁኔታ ትኩረት እንድትሰጡትና ድርድሩን ወደ መጨረሻ የሚወስድ ሚዛናዊ አቋም ላይ እንዲደረስ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የጀርመን ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና የአውሮፓ ህብረት ገንቢ ለሆነው ትብብርና ለብሔራዊ ሉአላዊነት ክብር ያደረጋችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ መንግስትና የአውሮፓ ህብረት በአሁኑ ወቅት የኮቭድ-19 የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር እና ወቅታዊ ሁኔታ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወረርሽኙን ለመዋጋትና ለልማት ላደረጋችሁት ድጋፍ እናመሰግናለን፡፡ በመጨረሻም ለጀርመን የመገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ ዘገባም እንዲሁ እናመሰግናለን፡፡

ከከበረ ሠላምታ ጋር
ፕሮፌ. ዶ/ር አስናቀች ላስ-ስዩም ፣
በቴክኒካል ኬሚስትሪ ፕሮፌሰር፣ በርሊን፤ በኢትዮጵያ ባሌ የትምህርት ቤቶች ከፍተኛ አስተባባሪ፣ ከአዲስ አበባ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዕውቀት ሽግግር ዙርያ በተለይ በኢነርጂና ታዳሽ ኃይል ላይ የሚሰሩ
ዶ/ር ጸጋዬ ደግነህ፣
ኢኮኖሚስት፣ በጀርመንና ኢትዮጵያ መካከል የዕውቀት ሽግግርና፣በትልቅ ኮርፖሬሽን የህብረ-ብሄራዊነት አስተዳደር ላይ የሚሰሩ፣ በዓለምአቀፍ ሰፖርት ማህበር የስነ-ምግባር ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት
ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም


Share

Published

Updated


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
"የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር ተደናግጠናል" በጀርመን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት | SBS Amharic