Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚሠሩበት የሜልበርን የእርድ ሥጋ ማዘጋጃ ፋብሪካ ጋር በተያያዘ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 49 ደረሰ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኙ ሜልበርን ከሚገኘው የእርድ ሥጋ ማዘጋጃ ፋብሪካ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተያያዘው ከአንድ ወር በፊት አንድ ሠራተኛ ሥራ ላይ ባልነበረበት ወቅት በቫይረሱ ተጠቅቶ ሳለ መሆኑን "The Australian" ሪፖርት አደረገ።

Melbourne meatworks coronavirus cluster grows to 49 as new infections confirmed
کارخانه تولید گوشت سیدر اکنون به کانون جدید ویروس کرونا در ویکتوریا تبدیل شده است. Source: AAP

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ መጤዎች የሚሠሩበት ብሩክሊን - ሜልበርን ካለው ሲዳር ሥጋዎች ፋብሪካ ጋር በተገናኘ ትናንት ማምሻውን አራት ሰዎች በተጨማሪ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አክሎ 49 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ታውቋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በእርድ ሥጋ ማዘጋጃው የቫይረሱ መከሰት የታወቀው ኤፕሪል 2 ቢሆንም፤ ያ አሁን ተከስቶ ካለው የወረርሽኙ መዛመት ጋር ተያያዥነት እንዳለው በባለ ሥልጣናት ዘንድ አልታመነበትም።

ሆኖም ቫይረሱ ለሁለተኛ ጊዜ ኤፕሪል 24 ተከስቷል።

እንዲያም ሆኖ እስከ ኤፕሪል 29 ድረስ በዲፓርትመንቱ በኩል ሁሉንም ሠራተኞች እንዲመረመሩ ማድረጉን ጨምሮ ታካይ እርምጃዎች አልተወሰዱም። 

ማክሰኞ ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ 17 ሰዎች በኮቪድ - 19 መያዛቸው ሲገለጥ 11ዱ የሲዳር ሥጋዎች ፋብሪካ ሠራተኞች ናቸው።

የቪክቶሪያ ዋና የጤና ኃላፊ ፕሮፌሰር ብሬት ሳቶን ቫይረሱ ተስፋፊነቱ ቢያዘግምም አለመክሰሙን ሲያስገነዝቡ፤

"በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መጨመር ዳግም ልብ የሚያሰኘን ምንም እንኳ የቫይረሱ ተዛማችነት እያሽቆለቆለ ቢሔድም፤ ከኮቪድ - 19 ጋር የምናደርገው ፍልሚያ ለፍጻሜ የተቃረበ አለመሆኑን ነው" ብለዋል።  

ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በጤና ጠበብት ምክረ ሃሳብ መሠረት እስከ ሜይ 11 የማኅበራዊ ርቀት ገደቦች ጸንተው እንዲቆዩ ባሳለፉት ውሳኔ ጸንተዋል።

Melbourne meatworks coronavirus cluster grows to 49 as new infections confirmed
Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP

የብሔራዊ ካቢኔው ተጥለው ያሉ ገደቦችን ለማላላትና ብሔራዊ መርሃ ግብሮችን ለመዘረጋት የፊታችን ዓርብ ይታደማል።  

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now